የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቢሾፍቱ ታሪካዊ የሰላም ቃል ኪዳን ተፈራረሙ
14:22 26.07.2025 (የተሻሻለ: 14:24 26.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቢሾፍቱ ታሪካዊ የሰላም ቃል ኪዳን ተፈራረሙ
ስምምነቱ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና በሰላም ሚኒስቴር ትብብር በተዘጋጀው ከፍተኛ የሰላም ጉባኤ ላይ የተገኘ ውጤት ነው።
የቃል ኪዳኑ ሰባት የስምምነት ነጥቦች፦
🟠 ሰላማዊ ፖለቲካ፣
🟠 የዲሞክራሲ ተቋማት እና እሴቶችን ማክበር፣
🟠 አካታችነትና ለብሔራዊ ጥቅም መቆም፣
🟠 ዲሞክራሲ እና መልካም አስተዳደርን ማስፈን፣
🟠 ለግጭት አያያዝ እና የሰላም ግንባታ ውጤታማነት መሥራት፣
🟠 ግልጽነትና የተጠያቂነት መርህ ማዳበር፣
🟠 ብሔራዊ ጥቅም እና ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ማጽናት።
ℹ ፓርቲዎቹ ፖለቲካዊ ልዩነቶች አንደተጠበቁ ሆነው ለሀገርና ለሕዝቡ ጥቅም ሲባል በኢትዮጵያ ሠላምን ለማስፈንና ለማጽናት በትጋት ለመሥራት እንተጋለን ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X