ዊሊያም ሩቶ 8ኛው የዓለም ድንቃድንቅ በሚባለው ማሳይ ማራ የቀጥታ ስርጭት አስጀመሩ

ሰብስክራይብ

ዊሊያም ሩቶ 8ኛው የዓለም ድንቃድንቅ በሚባለው ማሳይ ማራ የቀጥታ ስርጭት አስጀመሩ

የኬንያን የቱሪዝም ዘርፍ የማስተዋወቅ ግብ ያነገቡት የኬንያው ፕሬዝዳንት፤ በ2027 አምስት ሚሊየን ዓለም አቀፍ ቱሪስቶችን ለመሳብ ዘመቻ አስጀምረዋል።

ከታዋቂው የማሳይ ማራ የዱር እንስሳት ብሔራዊ መጠለያ የ2025 ታላቁ የአጋዘን መንጋ ፍልሰት የቀጥታ ስርጭት ላይ ሲናገሩ፤ ዘላቂ እና ለውጥ አብሳሪ ቱሪዝም ላይ ትኩረት ሰጥተዋል።

“እኛ ጎብኚውም ተቀባዩንም የሚያስደስት እና ተጓዦች የኬንያ አምባሳደር የሚሆኑበት ቱሪዝም ላይ እናተኩራለን” ብለዋል።

እ.ኤ.አ 2024 ኬንያን የሚጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር በ15% አድጎ 2.4 ሚሊየን የደረሰ ሲሆን 3.5 ቢሊየን ዶላር ገቢ አስገኝቷል። ዘመቻው የኬንያን የዱር እንስሳት፣ የባሕር ዳርቻ መዳረሻዎች በዓላት፣ ፈጠራ፣ ስፖርት እና ባሕላዊ ቅርሶች እንዲሁም የተለያዩ መስህቦችን ያስተዋውቃል።

ሩቶ ማሳይ ማራን የኬንያ ቱሪዝም “የዘውድ ጌጥ” ሲሉ ያሞካሹት ሲሆን፤ ዓመታዊው ታላቅ የፍልሰት ትዕይንት በመላው ዓለም አድናቆትን ያተረፈ እንደሆነ በአፅንኦት ተናግረዋል።

“ዘላቂ ቱሪዝም በማሳይ ማራ ሕያው ነው፤ ማኅበረሰቦች የሚጎለብቱበት፣ ሥነ-ምህዳሩ የሚያብብበት እና ተጓዦችም የሚደነቁበት ነው” ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0