"ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አፍሪካን መቆጣጠር ላይ ያነጣጠረ የፖለቲካ መሳሪያ ነው" - የማሊ የሕግ ባለሙያ
20:14 25.07.2025 (የተሻሻለ: 20:24 25.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አፍሪካን መቆጣጠር ላይ ያነጣጠረ የፖለቲካ መሳሪያ ነው" - የማሊ የሕግ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አፍሪካን መቆጣጠር ላይ ያነጣጠረ የፖለቲካ መሳሪያ ነው" - የማሊ የሕግ ባለሙያ
ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ምርመራዎቹን በአፍሪካ እና በመላው ደቡባዊው ዓለም ብቻ እንደሚያደርግ ዓለም ለብዙ ዓመታት ታዝቧል ሲሉ አማዱ ቲዩል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"በኢራቅ፣ ሊቢያ እና ፍልስጤም ውስጥ ከደረሰው የበለጠ አሰቃቂ ወንጀል የለም። ... ታዲያ አይሲሲ ይህን ወንጀል በፈፀሙ የመንግሥት መሪዎች ላይ ለምን እርምጃ አይወስድም?" ሲሉ ጠይቀዋል።
የቀድሞው የኮትዲቯር ፕሬዝዳንት ሎረንት ባግቦ ለአስር ዓመታት በእስር ላይ የቆዩበት መንገድ፤ "አይሲሲ የፖለቲካ መሳሪያ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው" ሲሉ የሕግ ባለሙያው ገልጸዋል።
ባግቦ፤ "እሳቸው ከተከሰሱበት እልቂት ጀርባ ፈረንሳይ እንደነበረች በይፋ ገልጸው የነበረ ቢሆንም፤ አይሲሲ ንጹህ መሆናቸው ከታወቀም በኋላ ምርመራ አላደረገም ሲሉ ጠበቃው አስታውሰዋል።
"አይሲሲ የተመሠረተባቸው የእኩልነት እሴቶች ተጥሰው፤ አሁን ግን ሀገራትን በአድሎ የሚያይ ፖሊሲ እንደነገሰ" ባለሙያው አክለዋል።
በዚህም የአፍሪካ ሀገራት የአይሲሲን ውጤታማነት እና ገለልተኝነት ለረጅም ጊዜ ጥያቄ ውስጥ ሲከቱ እና ፍርድ ቤቱ እንዲሻሻል ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል ሲሉ ቲዩል ተናግረዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X