የቴሌብር ቀጣናዊ ራዕይ!

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየቴሌብር ቀጣናዊ ራዕይ!
የቴሌብር ቀጣናዊ ራዕይ! - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.07.2025
ሰብስክራይብ

የቴሌብር ቀጣናዊ ራዕይ!

ኢትዮ ቴሌኮም ከሱዳንና ጅቡቲ ጋር ክልላዊ የክፍያ ትስስር ለመፍጠር እያካሄድው ያለው ድርድር፤ ኢትዮጵያ የቀጣናው ቁልፍ ተዋናይ እና በምሥራቅ አፍሪካ እንዲሁም በአህጉሪቱ የኢኮኖሚ ውህደት ጉልህ ሚና መጫወት እንደምትችል የሚያሳይ ነው።

🟠 የክፍያ ስርዓቱ ለሀገራቱ ምን ይፈይዳል? ቁልፍ ዝርዝር ጉዳዮች፦

ቀልጣፋ ግብይት፦ ትስስሩ በሀገራቱ መካከል የሚደረገውን ግብይት እስከ እጅ ስልክዎ ያሳጥራል፣

ተመጣጣኝ የአገልግሎት ክፍያ፦ በዓለም አቀፍ ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የሚፈጸሙ ግብይቶችን ያርቃል፣

በራስ ገንዘብ መገበያየት፦ ቴሌብርን ከፓን አፍሪካ የግብይት እና ክፍያ ስርዓት ጋር በማዋሃድ የሚቀርበው አገልግሎቱ፤ በሀገራቱ መካከል የሚደረገውን ግብይት ከዶላር ጥገኝነት ነፃ ሊያወጣ ይችላል።

ለምን ሱዳንና ጁቡቲ?

የሱዳን የዲጂታል የክፍያ ተቋማት በዓለም አቀፍ ደረጃ አገልግሎት የሚሰጡ በመሆኑ ከቴሌብር ጋር የሚኖረውን ጥምረት ያቀለዋል። ከኢትዮጵያ የገቢ ወጪ መስመር ጅቡቲ ጋር ኢኮኖሚያዊ ትስስርም ይበልጥ ይጠነክራል።

ኢትዮ ቲሌኮም በበጀት ዓመቱ በቴሌብር 2.38 ትሪሊየን ብር የተዘዋወረ ሲሆን አገልግሎቱ ከተጀመረ ጀምሮ በኢኮኖሚው ውስጥ 4.93 ትሪሊየን ብር ማዘዋወር ችሏል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0