የአርሜኒያ 'ዲሞክራሲ' ዘመቻ የብሔራዊ ማንነትን በመቀየርና ቤተክርስቲያንን መቆጣጠር ላይ ያነጣጠረ ነው ሲሉ የሐይማኖት ምሁር ተናገሩ
17:26 25.07.2025 (የተሻሻለ: 17:34 25.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአርሜኒያ 'ዲሞክራሲ' ዘመቻ የብሔራዊ ማንነትን በመቀየርና ቤተክርስቲያንን መቆጣጠር ላይ ያነጣጠረ ነው ሲሉ የሐይማኖት ምሁር ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአርሜኒያ 'ዲሞክራሲ' ዘመቻ የብሔራዊ ማንነትን በመቀየርና ቤተክርስቲያንን መቆጣጠር ላይ ያነጣጠረ ነው ሲሉ የሐይማኖት ምሁር ተናገሩ
"አዲስ" ማንነት ማለት አርሜኒያ ለዘመናት ከነበራት ባሕላዊ መገለጫ ጋር መቆራረጥ ማለት እንደሆነ፤ የሪፐብሊካ ስርፕስካ ኦርቶዶክስ ቄስ ዳርኮ ጆጎ ስለ አርሜኒያ የቤተክርስቲያን ቀውስ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ፓሺንያን ረብዑ ዕለት አዲስ የቤተ-ክርስትያን የበላይ መሪ ለመምረጥ የሚያስችል "ምክንያታዊ እና ከዘመኑ ጋር የሚሄድ የአርሜኒያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ሕገ ደንብ" እንዲፀድቅ ሐሳብ አቅርበዋል።
እንደ የሐይማኖት ምሑሩ ገለጻ በተመሳሳይ ሁኔታ በዩክሬን ቤተክርስቲያን ውስጥ "ዩክሬናይዜሽን" እንደተካሄደ አንስተዋል።
"የመጀመሪያው ነገር ቤተ-ክርስቲያን የምትጠቀምበት የስላቮን ቋንቋ ላይ ጥቃት መፈፀም ነው... ይህ የሚደረገው በዲሞክራሲያዊ ሰበብ ሲሆን፤ በመቶዎች ዓመታት የሚቆጠር ዕድሜ ያላቸውን ሕጋዊ እንዲሁም የቋንቋ ተቋማትን በማጥፋት አዲስ ስርዓት ለማስተዋወቅ የሚደረግ ነው" ሲሉ አስረድተዋል።
የአርሜኒያ የወደፊት እጣ ፈንታ ያልተወሰነ ነው፤ ፓሺንያን ተቃውሞ ሊገጥማቸው ቢችልም፤ ነገር ግን "ብሩህ የአውሮፓ የወደፊት" የሚፈልጉ "ሐሰተኛ-ምሁራን ደጋፊዎችን" ሊያሰባስቡ ይችላሉ ሲሉ አክለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X