በምግብ ራስን ለመቻል እንደ እንሰት ላሉ አካባቢያዊ ምግቦች ትኩረት መሥጠት እንደሚገባ ተመራማሪው አስታወቁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበምግብ ራስን ለመቻል እንደ እንሰት ላሉ አካባቢያዊ ምግቦች ትኩረት መሥጠት እንደሚገባ ተመራማሪው አስታወቁ
በምግብ ራስን ለመቻል እንደ እንሰት ላሉ አካባቢያዊ ምግቦች ትኩረት መሥጠት እንደሚገባ ተመራማሪው አስታወቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.07.2025
ሰብስክራይብ

በምግብ ራስን ለመቻል እንደ እንሰት ላሉ አካባቢያዊ ምግቦች ትኩረት መሥጠት እንደሚገባ ተመራማሪው አስታወቁ

እንሰት የአካባቢ ማሕበረሰብን የምግብ ጥገኝነት መቀነስ የሚያስችል በተለያየ መንገድ ለምግብነት መዋል የሚችል ተክል እንደሆነ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር አዲሱ ፍቃዱ

ለስፑትኒክ አፍሪካ በሠጡት ቃል ተናግረዋል። ተመራማሪው የእንሰት ልማት ስትራቴጂ ይፋ መደረጉን አስመልክቶ በሠጡት አስተያየት ተክሉ ከምግብነት ባለፈ ለአፈር እና ውሃ ጥበቃ አስተዋጽኦው የጎላ ነው ብለዋል።

"ለእንሰት ምርት ምንም አይነት ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ አናስመጣም... ስለዚህ በምግብ አቅርቦት ራሳችንን መቻል ከፈለግን እንደ እንሰት ባሉ በሀገር ውስጥ በሚገኙ የምግብ ምንጮች ላይ መተማመን አለብን።"

እንሰትን ድርቅ ወደሚያጠቃቸው አካባቢዎች በተለይም ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እና የአፍሪካ ሀገራት ለማዳረስ እንቅስቃሴ መጀመሩንም ገልፀዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0