አፍሪካ በአብዛኛው ከጥራት በታች በሆነ የውጭ ነዳጅ ግዢ፤ በየዓመቱ 90 ቢሊየን ዶላር ታጣለች ሲሉ አሊኮ ዳንጎቴ አስጠነቀቁ
17:08 24.07.2025 (የተሻሻለ: 17:14 24.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካ በአብዛኛው ከጥራት በታች በሆነ የውጭ ነዳጅ ግዢ፤ በየዓመቱ 90 ቢሊየን ዶላር ታጣለች ሲሉ አሊኮ ዳንጎቴ አስጠነቀቁ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አፍሪካ በአብዛኛው ከጥራት በታች በሆነ የውጭ ነዳጅ ግዢ፤ በየዓመቱ 90 ቢሊየን ዶላር ታጣለች ሲሉ አሊኮ ዳንጎቴ አስጠነቀቁ
አፍሪካ በቂ ድፍድፍ ነዳጅ እያመረተች ቢሆንም በየዓመቱ ከ85 በመቶ በላይ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት፤ ከ120 ሚሊየን ቶን በላይ የተጣሩ የነዳጅ ምርቶችን ከውጭ ለማስገባት ይወጣል ብለዋል ናይጄርያዊው ቢሊየኔር፡፡
በአቡጃ በተካሄደው የምዕራብ አፍሪካ የተጣራ ነዳጅ ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ያደረጉት ባለሃብቱ፤ "በየዓመቱ የአህጉሩን አጠቃላይ የኢኮኖሚ አቅም ለሌሎች እያስተላለፍን ነው" ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
እንደ ዳንጎቴ አገላለጽ አፍሪካ የኃይል ነጻነቷን ለማግኘት ምን መሰናክሎችን ማለፍ ይኖርባታል?
◻ አፍሪካ የተጣሩ የነዳጅ ምርቶችን በራሷ "የማምረት በቂ አቅም አላት"፤ ነገር ግን ከዕለታዊ የተጣራ ምርት ፍጆታዋ ውስጥ 40 በመቶ ያህሉን ብቻ የምታጣራ በመሆኑ፤ ርካሽ እና አብዛኛውን ጊዜ መርዛማ ለሆኑ የውጭ ነዳጆች መንገድ ከፍቷል።
◻ የአፍሪካ የነዳጅ ማጣሪያዎች የናይጄሪያን ድፍድፍ ነዳጅ ከአምራቾች በቀጥታ ከመግዛት ይልቅ በዓለም አቀፍ ነጋዴዎች በኩል በመግዛታቸው ተጨማሪ ክፍያዎችን ይከፍላሉ።
◻ የምዕራብ አፍሪካ ከፍተኛ የወደብ ክፍያዎች (እስከ 40% የሚደርስ) ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲነጻጸር አላግባብ ውድ ናቸው።
◻ የተለያዩ ብሔራዊ የነዳጅ ደረጃዎች በአህጉሪቱ ውስጥ የሚደረገውን የድንበር ተሻጋሪ የተጣራ የነዳጅ ምርት ንግድን ያግዳሉ።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X