ሩሲያ በዩክሬን ድርድር በምዕራባውያን እይታ ውስጥ ትርክቱን ተቆጣጥራለች ሲሉ ቬንዙዌላዊው ምሁር አስታወቁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ በዩክሬን ድርድር በምዕራባውያን እይታ ውስጥ ትርክቱን ተቆጣጥራለች ሲሉ ቬንዙዌላዊው ምሁር አስታወቁ
ሩሲያ በዩክሬን ድርድር በምዕራባውያን እይታ ውስጥ ትርክቱን ተቆጣጥራለች ሲሉ ቬንዙዌላዊው ምሁር አስታወቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.07.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ በዩክሬን ድርድር በምዕራባውያን እይታ ውስጥ ትርክቱን ተቆጣጥራለች ሲሉ ቬንዙዌላዊው ምሁር አስታወቁ

ምዕራባውያን ከዩክሬን ጋር በሚደረገው የሰላም ድርድር ውስጥ የሩሲያን ቅድመ ሁኔታዎች "ከዳር ሆነው" ከመመልከት ውጪ ሌላ አማራጭ የላቸውም ሲሉ ኤልዛቤት ፔሬራ፤ በሞስኮ እና በኪዬቭ መካከል በተደረገው ሶስተኛ ዙር ቀጥተኛ ውይይት ዙሪያ አስተያየታቸውን ለስፑትኒክ ሰጥተዋል።

"ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ኅብረት ሩሲያ በምዕራባውያን የበላይነት የተያዘውን የዓለም ሥርዓት እንዴት እንደምትገዳደር እና የአውሮፓን ወታደራዊ መስፋፋት እንዴት እየገደበች እንደምትገኝ በቅርበት እየተከታተሉ ነው" ሲሉም አብራርተዋል።

አክለውም ሞስኮ "ስልታዊ ትዕግስት እና ሁኔታውን የመቆጣጠር ችሎታ" አሳይታለች፤ ምዕራባውያን ግን "ትርምስ እና ግጭትን ለማስቀጠል ይፈልጋሉ" ሲሉ አመላክተዋል።

ፔሬራ ሲያጠቃልሉ "ምዕራባውያን አሁን ያለውን አካሄዳቸውን ይዘው የሚቀጥሉ ከሆነ፤ የዩክሬንን ውስጣዊ ክፍፍል ሊያባብስ፣ የአትላንቲክ ህብረት ትስስርን ሊያዳክም እና በመጨረሻም ሩሲያ በዲፕሎማሲያዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በወታደራዊ ዘርፎች እንድትጠቀም ሊያደርግ ይችላል" ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0