የኪዬቭ ባለሥልጣናት ከሞስኮ ጋር ለመስማማት ቅንነት ይጎድላቸዋል ሲሉ የሩሲያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ገለጹ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኪዬቭ ባለሥልጣናት ከሞስኮ ጋር ለመስማማት ቅንነት ይጎድላቸዋል ሲሉ የሩሲያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ገለጹ
የኪዬቭ ባለሥልጣናት ከሞስኮ ጋር ለመስማማት ቅንነት ይጎድላቸዋል ሲሉ የሩሲያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ገለጹ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.07.2025
ሰብስክራይብ

የኪዬቭ ባለሥልጣናት ከሞስኮ ጋር ለመስማማት ቅንነት ይጎድላቸዋል ሲሉ የሩሲያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ገለጹ

"በቅርብ ጊዜ የዩክሬን ባለሥልጣናት የፈፀሟቸውን ድርጊቶች እና መግለጫዎች ስንገመግም በድርድሩ ከልባቸው እየተሳተፉ አይደለም ለማለት ያስችላናል” ሲሉ ቫለንቲና ማትቪየንኮ ተናግረዋል።

ተጨባጭ ጉዳዮች ላይ በቁም ነገር ተነጋግሮ መሻሻሎች ይኖራሉ ተብሎ ለመጠበቅ ጊዜው ገና ቢሆንም፤ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የሚደረገው ድርድር ጠቃሚ በመሆኑ መቀጠል አለበት ሲሉ ባለሥልጣኗ አመልክተዋል።

ሩሲያ ዩናይትድ ስቴትስ የዩክሬን ቀውስ መንስኤዎችን እንድትረዳ እንደምትፈልግና ይህም ጊዜ እና ትዕግስት እንደሚጠይቅ ጨምረው ገልጸዋል።

በተጨማሪም የሞስኮ እና ዋሽንግተን ግንኙነት በዓለም ፖለቲካ አውድ "ሰፊ ገጽታ" ያለው በመሆኑ በዩክሬን ዙሪያ ብቻ ሊያጠነጥን አይገባም ብለዋል ማትቪየንኮ፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0