ካምቦዲያና ታይላንድ ውጥረት ውስጥ ገብተዋል፡፡ ክስተቱን በተመለከተ እስካሁን የተሠሙ ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ

ካምቦዲያና ታይላንድ ውጥረት ውስጥ ገብተዋል፡፡ ክስተቱን በተመለከተ እስካሁን የተሠሙ ዜናዎች፦

ሁለቱ ሀገራት በሚጋጩበት ድንበር አካባቢ ወታደሮች ተኩስ መለዋወጣቸውን ተከትሎ ዛሬ ጠዋት ግጭት መከሰቱ ተዘግቧል። ሁለቱም ወገኖች አስቀድሞ ተኩስ በመክፈት ረገድ አንዱ ሌላውን ከሷል።

▪የታይላንድ የጤና ሚኒስቴር በካምቦዲያ ጥቃት በትንሹ 11 ሲቪሎች መገደላቸውን ገልጿል፡፡

▪ታይላንድ ካምቦዲያ በቢኤም-21 ግራድ ባለብዙ ሮኬት ማስወንጨፊያ ሲስተሞች በሲቪል ኢላማዎች ላይ ጥቃት ፈጽማለች ብላለች፡፡

▪የካምቦዲያ ኃይሎች ከታይላንድ ወታደራዊ ጣቢያ 200 ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ፕራሳት ታ ሙየን ቶም ቤተ-መቅደስ ላይ ተኩስ ከፍተዋል ሲል የታይላንድ ጦር ገልጿል፡፡

▪የታይላንድ አየር ኃይል ኤፍ-16 የጦር ጄቶች የካምቦዲያ ጦር ይዞታን አጥቅተዋል፡፡

▪የካምቦዲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ታይላንድ በድንበር አካባቢ በሚገኙ የካምቦዲያ ይዞታዎች ላይ "ጠብ አጫሪ እና ሆን ተብሎ የተቀነባበሩ ጥቃቶችን" ፈጽማለች ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

▪ታይላንድ ከካምቦዲያ ጋር ያላትን የድንበር መተላለፊያ ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ዘግታለች፤ በተጨማሪም ከካምቦዲያ ጋር በሚዋሰኑ አራት ግዛቶቿ ውስጥ የሚኖሩ ዜጓቿ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አዛለች፡፡

▪በፕኖም ፔን የሚገኘው የታይላንድ ኤምባሲ በዛሬዎ ዕለት በካምቦዲያ የሚገኙ ዜጎች ለቀው እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

▪ሁለቱም ሀገራት በድንበር አካባቢ ያሉ ይዞታዎቻቸውን እያጠናከሩ ነው፡፡

▪የታይላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪስ ሳንጊያምፖንግሳ በዛሬው ዕለት ከተመድ ዋና ጸሐፊ እንዲሁም ከጃፓን፣ ከሩሲያና ከሌሎች ሀገራት ተወካዮች ጋር እየተባባሰ የመጣውን ግጭት አስመልክቶ ውይይት ያደርጋሉ።

▪የካምቦዲያ ጠቅላይ ሚኒስትር የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ከታይላንድ ጋር በተፈጠረው ግጭት ዙሪያ "አስቸኳይ ስብሰባ" እንዲጠራ ጠይቀዋል።

ውጥረቱ የጀመረው ግንቦት 20 በአከራካሪው ገለልተኛ ቀጣና በታይላንድ እና በካምቦዲያ ወታደሮች መካከል ከተፈጠረው ግጭት በኋላ ነው።

ከማህበራዊ የትስስር ገፆች የተገኙ ምስሎች

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0