ሩሲያ ቢያንስ 1 ሺህ 200 የጦር እስረኞችን ለመለዋወጥ ለዩክሬን ሃሳብ አቀርበች

ሩሲያ ቢያንስ 1 ሺህ 200 የጦር እስረኞችን ለመለዋወጥ ለዩክሬን ሃሳብ አቀርበች
የሩሲያ የልዑካን ቡድን መሪ ሜዲንስኪ ከዩክሬን ጋር ከተካሄደው ሶስተኛው ዙር ድርድር በኋላ ለፕሬስ በሰጡት መግለጫ የገለፁት ነው።
ተጨማሪ መግለጫዎች፦
በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል በተደረገው የሁለተኛው ዙር ድርድር ሁሉም የሰብዓዊነት ስምምነቶች ተፈጽመዋል፣
በሩሲያ እና በዩክሬን ታይቶ የማይታወቅ ትልቅ የእስረኞች ልውውጥ ተጠናቋል፣
ሩሲያ በኦንላይን የሚሠሩ ሶስት የሥራ ቡድኖች እንዲቋቋሙ ለዩክሬን ሃሳብ አቅርባለች፣
ሩሲያ ተጨማሪ 3 ሺህ የሞቱ የዩክሬን ወታደሮችን ለኪዬቭ ለማስረከብ ሃሳብ አቅርባለች፣
በጦር ግንባር ላይ በከባዱ በቆሰሉ እና በታመሙ ዙሪያ የሚካሄደው የሕክምና ልውውጥ ይቀጥላል፣
ኪዬቭ በዩክሬን የተያዙ የኩርስክ ክልል ሲቪሎችን ሁኔታ ግልጽ ማድረግ አለባት፣
ሩሲያ እና ዩክሬን በድርድሩ ሰነዶቹ ላይ በተገለጹት አቋሞች ዙሪያ ረጅም ጊዜ አሳልፈዋል፤ አቋማቸው በጣም የተራራቁ ናቸው፣
ሩሲያ በመጨረሻው ዙር ድርድር የተረከበችውን የዩክሬን ህፃናትን ዝርዝር ላይ ሥራ አጠናቃለች፣
ሩሲያ ኪዬቭ ወደ ዩክሬን የተወሰዱ የሩሲያ ህፃናትን እንድትመልስ ጥያቄ አቅርባለች፣
የሩሲያ እና ዩክሬን መሪዎች ስብሰባ የግጭቱን መቆም ማብሰር አለበት። በመሪዎቹ መካከል ከሚደረገው ስብሰባ በፊት የስምምነቱ ሁኔታዎች ላይ መግባባት ያስፈልጋል እንዲሁም በስብሰባው ላይ ምን እንደሚወያዩ ግልጽ መሆን አለበት፣
የሩሲያ የሰብዓዊ መብት እና የህጻናት መብት ኮሚሽነሮች በሩሲያ ግዛት ውስጥ አሉ የተባሉ የዩክሬን ህጻናት ስም ዝርዝርን እየመረመሩ ነው። በዩክሬን ዝርዝር ውስጥ ያሉ ብዙ ህፃናት በሩሲያ ግዛት ውስጥ ገብተው አያውቁም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X