"አፍሪካ ምን አይነት ሥርዓተ ምግብ መከተል እንዳለባት፤ የግብርና ሥነ-ምሕዳሯ እንጂ ሌሎች ሊወስኑላት አይገባም"

ሰብስክራይብ

"አፍሪካ ምን አይነት ሥርዓተ ምግብ መከተል እንዳለባት፤ የግብርና ሥነ-ምሕዳሯ እንጂ ሌሎች ሊወስኑላት አይገባም"

የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ኅብረት ዋና አስተባባሪ ሚሊዮን በላይ፤ በመዲናዋ እየተካሄደ ካለው የአፍሪካ የሥርዓተ ምግብ ፖሊሲ የምክክር መድረክ ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ የተናገሩት ነው።

"ከሥርዓተ ምግብ ቅኝ ግዛት ነፃ መውጣት የምንችልበት ብቸኛው መንገድ፤ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛቶች እና ዘረኛ ርዕዮተ ዓለሞች እንዴት ነው የአሕጉሪቱን ሥርዓተ ምግብ እየጎዱ ያሉት የሚለውን በግልጽ መነጋገር ስንችል ነው" ብለዋል።

ጉባኤው በአሕጉሪቱ የምግብ ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ በሚያስችሉ ስልቶች ላይ ትኩረቱን አድርጎ በመምከር ላይ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0