አርሜኒያ ስትራቴጂያዊ የኮሪደር መተላለፊያዋን ለአሜሪካ ማስረከቧ የጂኦፖለቲካዊ ስጋት ቀሰቀሰ

አርሜኒያ ስትራቴጂያዊ የኮሪደር መተላለፊያዋን ለአሜሪካ ማስረከቧ የጂኦፖለቲካዊ ስጋት ቀሰቀሰ
የስፔን ፔሪዮዲስታ ዲጂታል እንደዘገበው አርሜኒያ ከአዘርባጃን ናኪቼቫን ወደምትባለው ግዛት በሲዩኒክ ክልል በኩል በሚያገናኘው መተላለፊያ፣ የ "ትራምፕ ድልድይ ትራንስፖርት ኮሪደር" ለመፍጠር ከአሜሪካ ጋር የ99 ዓመት ምሥጢራዊ ስምምነት ተፈራርማለች፡፡
ዐቢይ እውነታዎች፦
🟡 የ42 ኪሎ ሜትር መተላለፊያው በአሜሪካ የግል ኩባንያ የሚመራ ሲሆን የአሜሪካው ኩባንያ 40 በመቶ የሚሆነውን ገቢ ሲከት አርሜኒያ 30 በመቶ ብቻ ታገኛለች፡፡ እንዲሁም መስመሩ በ1 ሺህ የአሜሪካ ወታደራዊ ቅጥረኞች ይጠበቃል፡፡
🟡 ኮሪደሩ በአዘረባጃን እና በማኪቼቫን መካከል ያልተገደበ የሰዎች፣ የተሽከርካሪ እና የሸቀጥ መተላለፍን የሚጠይቀው የባኩ የ2020 የተኩስ አቁም ስምምነት ጥያቄን ያሟላል፡፡
🟡 አሜሪካ የመቶ ዓመት የሊዝ ሀሳብን በይፋ ስትናገር የነበረ ሲሆን በቱርክ የአሜሪካ አምባሳደር ቶም ባራክ የዩናይትድ ስቴትስ “ትረከበው” ሲሉም ተሠምተዋል።
ለምን አወዛጋቢ ሆነ?
🟡 ውሉ አርሜኒያ ከኢራን ጋር በምትጋራው ወሳኝ የድንበር አካባቢ ላይ ያላትን ሉዓላዊነት ያኮስሳል፡፡
🟡 ኢራን ኮሪደሩ የካውካሰስ አካባቢ ተጋላጭነቷን የሚያሳጣት አደጋ አድርጋ ትመለከተዋለች፤ እንዲሁም በአሜሪካ፣ በእስራኤል እና በዘረ-ቱርክ ኃይሎች የመከበብ ስጋት አላት፡፡
🟡 የሩሲያ እና ኢራን ሰሜን-ደቡብ ትራንስፖርት መተላለፊያን በማዳከም ተጽዕኖ እና ንግድን ከቁልፍ የቀጣናው ተዋናዮች ሊያርቅ ይችላል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X