🫘 የኢትዮጵያ አርሶ አደሮችን አመድ አፋሽ ሲያደረጉ የነበሩ የባቄላ ሥር አበስባሽ አፈር ወለድ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን በምርምር ተገኙ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ🫘 የኢትዮጵያ አርሶ አደሮችን አመድ አፋሽ ሲያደረጉ የነበሩ የባቄላ ሥር አበስባሽ አፈር ወለድ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን በምርምር ተገኙ
🫘 የኢትዮጵያ አርሶ አደሮችን አመድ አፋሽ ሲያደረጉ የነበሩ የባቄላ ሥር አበስባሽ አፈር ወለድ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን በምርምር ተገኙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.07.2025
ሰብስክራይብ

🫘 የኢትዮጵያ አርሶ አደሮችን አመድ አፋሽ ሲያደረጉ የነበሩ የባቄላ ሥር አበስባሽ አፈር ወለድ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን በምርምር ተገኙ

አፈር ወለድ በሽታዎች ለኢትዮጵያ ባቄላ ሰብል ምርት ኪሳራ ዋና ምክንያት ናቸው፡፡ አርሶ አደሮች በእያንዳንዱ የምርት ዘመን ከ45 እስከ 70 በመቶ የሚሆነውን ምርታቸውን በሥር አበስባሽ በሽታ ያጣሉ፡፡

ተመራማሪዎች የሥር በሽታን በመመርመር እና ከሰባት ዋና ዋና አምራች ክልሎች 150 የባቄላ ማሳዎች የአፈር ናሙናዎችን ሰብስበው አጥንተዋል፡፡

የጥናቱ ዋና ዋና ግኝቶች፦

በስፋት የተሰራጩ በሽታ አምጪ የአፈር ተህዋሲያን፣

ከፍተኛ መጠን ያለው የቅጠል በሽታ፣

ለተክሎች ጤና ከፍተኛ ስጋት የሆነው ሥር-አቁሳይ ኔማቶድ ትል፣

የሥር አበስባሽ በሽታ መጠን እና አይነት ታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት መሪነት፣ የአምስት ዓለም አቀፍ የምርምር ማዕከላት ተመራማሪዎች ያደረጉት ይህ ጥናት ፓቶጅንስ ጆርናል ላይ ታትሞ ወጥቷል፡፡

ከአውስትራሊያ ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ የግብርና እና አካባቢ ትምህርት ቤት እና የግብርና ኢንስቲትዩት ፕ/ር እና የጥናት ቡድኑ አባል ማርቲን ባርቤቲ "በአፈር ወለድ በሽታዎች ውስጥ የሚገኙ በሽታ አምጪ ተህዋሲያንን በአስተማማኝ እና በትክክል የመለየት አቅም እነሱን ለመተንበይ እና ለመቆጣጠር በመሠረታዊነት አስፈላጊ ነው" ይላሉ፡፡

ግኝቶቹ ለአካባቢው የአፈር እና የአየር ንብረት ሁኔታዎች ተስማሚ እና ተቋቋሚ የሆኑ የባቄላ ዝርያዎችን በመለየት ተገቢ የእርሻ ልምዶችን ጨምሮ የተቀናጀ የበሽታ አስተዳደር አካሄዶችን ይጠይቃሉ፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0