አፍሪካን ከምግብ ቅኝ ግዛት ነፃ ለማውጣት፤ ህዝቦች ወደ ቀደመ የምግብ ሥርዓታቸው እንዲመለሱ ማበረታታት ይገባል - ዚምቧቤያዊው ሼፍ

ሰብስክራይብ

አፍሪካን ከምግብ ቅኝ ግዛት ነፃ ለማውጣት፤ ህዝቦች ወደ ቀደመ የምግብ ሥርዓታቸው እንዲመለሱ ማበረታታት ይገባል - ዚምቧቤያዊው ሼ

ታፋድዝዋ አኒፋሲ የትውልዱን ስርዓተ ምግብ በማስተካከል የአህጉሪቱ አርሶ አደሮች ለጤና ተስማሚ የሆኑ ባህላዊ ምግቦችን ይበልጥ ማምረት እንዲችሉ አመቺ ነባራዊ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባም፤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ከሚገኘው የአፍሪካ ሼፎች ጉባኤ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጿል።

"እንደማስበው ባህላዊ ምግቦቻችንን እንደገና ለማስተዋወቅ ብዙ ማድረግ ያሉብን ነገሮች አሉ። የሰዎች የምግብ ምርጫ ወደ ፈጣን፣ ተፈትገው ወደ ሚዘጋጁ እና ሱካር ወደሚበዛባቸው ምግቦች እየተቀየረ መጥቷል። ሰዎች ወደ በፊት አመጋገባቸው እንዲመለሱ ማንቃት ያስፈልጋል" ብሏል።

"ምግቤ አፍሪካዊ ነው" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው በዚህ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የምግብ ባለሙያዎች፣ የምግብ አምራቾች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0