ቤልጀም እና ሉግዘምበርግ በሳሕል ጥምረት ሀገራት ውስጥ ያላቸውን ኢንቨስትመንት እንደሚቀነሱ ዘገባዎች ጠቆሙ
16:55 23.07.2025 (የተሻሻለ: 17:04 23.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቤልጀም እና ሉግዘምበርግ በሳሕል ጥምረት ሀገራት ውስጥ ያላቸውን ኢንቨስትመንት እንደሚቀነሱ ዘገባዎች ጠቆሙ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቤልጀም እና ሉግዘምበርግ በሳሕል ጥምረት ሀገራት ውስጥ ያላቸውን ኢንቨስትመንት እንደሚቀነሱ ዘገባዎች ጠቆሙ
የቤልጀም የዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ኢናቤል፣ የቤልጀም የታዳጊ ሀገራት የኢንቨስትመንት ኩባንያ እና የሉግዘምበርግ የልማት ትብብር ኤጀንሲ እስከ 2025 የመጨረሻ ሩብ ዓመት ድረስ ካፒታላቸውን እና ሠራተኞችን ከጥምረቱ ሀገራት ለማስወጣት እየተዘጋጁ መሆናቸውን የፈረንሳይ ሚዲያ ዘግቧል።
በሳሕል ያለው የፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም በአውሮፓ እና በጥምረቱ መካከል የተፈጠረው የፖለቲካ ግንኙነት መቋረጥ የውሳኔው ምክንያቶች መሆናቸውን ዘገባው አመላክቷል፡፡
በ2024 የተቋቋመው አዲሱ የምዕራብ አፍሪካ ቀጣናዊ ጥምረት፤ ሉዓላዊነትን ለማጠናከር ብሎም ደህንነትን እና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ጨምሮ በልዩ ልዩ ዘርፎች በቀድሞ ቅኝ ገዥዎች ላይ የነበረውን ጥገኝነት መቀነስ ዋና ግቡ ነው፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X