በአፍሪካውያን እና በአፍሪካ አሜሪካውያን ወጣቶች ላይ የወትሮውን ምርመራ ሂደት የሚፈታተን አዲስ ንዑስ የስኳር በሽታ ዓይነት ተገኘ

በአፍሪካውያን እና በአፍሪካ አሜሪካውያን ወጣቶች ላይ የወትሮውን ምርመራ ሂደት የሚፈታተን አዲስ ንዑስ የስኳር በሽታ ዓይነት ተገኘ
ወሳኙ ግኝት፦ በላንሴት የስኳር ሕመም እና ኢንዶክሪኖሎጂ የታተመው ጥናት በሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ወጣቶች ላይ እንዲሁም በከፊል ጥቁር አሜሪካውያን ላይ የሰውነት መከላከያ አቅም መነሻ ያልሆነ ታይፕ 1 የስኳር በሽታ ዓይነት መታየቱን አረጋግጧል፡፡
በምን ይለያል?
ከተለመደው ታይፕ 1 የስኳር በሽታ በተለየ መልኩ፣ በጥናቱ ውስጥ ከተሳተፉት አፍሪካውያን መካከል 65 በመቶዎቹ ኢንሱሊን ለሚያጠቃው የስኳር በሽታ ዋና ምልክቶች የሆነው አይሌት ኡውቶአንቲቦዲ አልተገኘባቸውም፡፡ እነዚህ ወጣቶች ታዲያ ታይፕ 1 የስኳር በሽታ ሊኖርባቸው በመቻሉ የተለየ የምርመራ እና የሕክምና ዘዴዎች ያስፈልጋቸዋል፡፡
ከአሜሪካ ንጽጽር፡-
ተመራማሪዎች በተጨማሪም የስኳር በሽታ ያለባቸው 15 በመቶ ጥቁር አሜሪካውያን ከፈረንጅ አቻዎቻቸው በተቃራኒ አውቶአንቲቦዲ ነጋቲቭ እና ከተለመደው በተለየ ዘረመል ተመሳሳይ ቅርፅ አሳይተዋል፡፡
ለምን ይገዳል?
ይህ ካሜሩን፣ ዩጋንዳ፣ ደቡብ አፍሪካ እና አሜሪካን ያካለለው ጥናት፤ ቀደም ሲል በተለመዱ አሠራሮች በቂ አገልግሎት ያላገኙ ሕዝቦችን ይበልጥ ትክክለኛ ምርመራ እና ግላዊ የሕክምና ክብካቤ ስልቶችን ወደ ማግኘት ሊመራ ይችላል፡፡
"በእነዚህ ግለሰቦች ስብስብ ውስጥ አማራጭ መንስኤዎች መታየት አለባቸው፤ እናም የዚህን ንዑስ ዓይነት መነሻዎችን መረዳት ለመከላከል እና ለሕክምና አዳዲስ ግንዛቤዎችን ሊሰጥ ይችላል" ሲል ጥናቱ አመልክቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X