በኢትዮጵያ ከተቋማዊ ይልቅ ማኅበረሰባዊ የእርቅ ሥርዓቶች ተቀባይነት እያገኙ መሆኑን ሰላም ሚኒስቴር ገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበኢትዮጵያ ከተቋማዊ ይልቅ ማኅበረሰባዊ የእርቅ ሥርዓቶች ተቀባይነት እያገኙ መሆኑን ሰላም ሚኒስቴር ገለፀ
በኢትዮጵያ ከተቋማዊ ይልቅ ማኅበረሰባዊ የእርቅ ሥርዓቶች ተቀባይነት እያገኙ መሆኑን ሰላም ሚኒስቴር ገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.07.2025
ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ ከተቋማዊ ይልቅ ማኅበረሰባዊ የእርቅ ሥርዓቶች ተቀባይነት እያገኙ መሆኑን ሰላም ሚኒስቴር ገለፀ

በአንዳንድ አካባቢዎች ከመንግሥት “ቅጣትና ሽልማት” ይልቅ ለማኅበረሰባዊው “የሰናይ እና እኩይ” እሳቤ ቅድሚያ የመሰጠት አዝማሚያ መኖሩን የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ቸሩጌታ ገነነ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

“የሽምግል እና ባሕላዊ የግጭት አፈታት እሴቶች በማኅበረሰቡ ዘንድ ተቋማዊ ከሆነው የግጭት አፈታት በጣም በላቀ ሁኔታ ተቀባይነት አላቸው” ያሉት ቸሩጌታ፤ “ግጭት በሚነሳባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ባሕላዊ ሥርዓቶችና እሴቶችን የመቀበል ሁኔታ እያደገ መጠቷል” ብለዋል፡፡

▪ስለዚህም ማኅበረሰቡ ለእሴቶቹ ዋጋ እንደመስጠቱ ሁለቱንም ማለትም ዘመናዊውንም ባህላዊውንም የግጭት አፈታት መንገድ በማቀናጀት ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ይደረጋል ሲሉ አክለዋል፡፡

▪ አሁን በጋምቤላ በባሕላዊ የእርቀ ሰላም የሚጠናቀቀውን ሂደት በአብነት ጠቅሰዋል፡፡

▪ ከዚህ በተቃራኒ ግን ከሰላማዊ መንገድ ውጭ ሰላም ማምጣት እንደማይቻል ነው አጽንዖት የሰጡት፡፡

“ልማትን እፈልጋለሁ ብለህ ከልማት ተቃራኒውን የምትሠራ ከሆነ፣ ሰላም ብለህ የምታስበበት መንገድ ደግሞ ሰላማዊ ካልሆነ፤ ፖለቲካ ልምምድህ ኃይልን መሠረት ያደረገ ከሆነ፤ ጦረኝነትን የምታበረታታ ከሆነ፤ በመንገዱና በግቡ መካከል ተቃርኖ አለና ሰላምን ልታመጣ አትችልም፡፡”

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0