ሞሮኮ በአፍሪካ ልማት ባንክ የ117 ሚሊየን ዶላር እገዛ፣ በግብርና ዘርፍ የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎን ለማሳደግ ወጥናለች
18:32 22.07.2025 (የተሻሻለ: 18:34 22.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሞሮኮ በአፍሪካ ልማት ባንክ የ117 ሚሊየን ዶላር እገዛ፣ በግብርና ዘርፍ የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎን ለማሳደግ ወጥናለች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሞሮኮ በአፍሪካ ልማት ባንክ የ117 ሚሊየን ዶላር እገዛ፣ በግብርና ዘርፍ የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎን ለማሳደግ ወጥናለች
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለሞሮኮ ሁሉን አቀፍ እና አንድነትን መሠረት ላደረገ የግብርና መርሃ ግብር ብድር አጽድቋል፡፡
ዐቢይ ግቦች፦
በግብርና ለሚሳተፉ ሴቶችና ወጣቶች ዘላቂ የኢኮኖሚ እድል ማመቻቸት፣
ሴቶችን ማሠልጠን እና በአግሪ እንዲሁም በግብርና ምርት ማቀነባበሪያዎች ላይ ያላቸውን ሚና ማሳደግ፣
የምግብ ዋስትናን ማሳደግ እና ለመደበኛ አምራች አርሶ አደሮች የአየር ንብረት ለውጥ የመቋቋም አቅም መገንባት፣
በተበጀተ የገንዘብ ድጋፍ የገጠር ሥራ ፈጣራን ማበረታታት፣
የሞሮኮ የ2020-2030 የአረንጓዴ ትውልድ ስትራቴጂን እና የወጣቶች ሥራ ፈጠራን መደገፍ ይገኙበታል፡፡
የአፍሪካ ልማት ባንክ የሞሮኮ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አሽራፍ ታርሲም፤ "በዚህ አዲስ ዘመቻ አማካኝነት ዘመናዊ፣ ሁሉን አቀፍና ጠንካራ ግብርና ለመገንባት፣ በአካባቢያቸው አዳዲስ ፈጠራዎችን ለመፍጠር፣ እሴት ለመጨመርና የሥራ እድል ለመፍጠር ለሚያልሙ ሴቶች ሁሉ ሙሉ አቅማቸውን እንዲያወጡ ደረጃ በደረጃ ድጋፍ እናደርጋለን" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X