ዓለም አቀፍ የሊቲየም ዋጋ በቀነሰበት ሁኔታ የዚምባብዌ የሊቲየም የወጪ ንግድ በ30 በመቶ ማደጉ ተነገረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዓለም አቀፍ የሊቲየም ዋጋ በቀነሰበት ሁኔታ የዚምባብዌ የሊቲየም የወጪ ንግድ በ30 በመቶ ማደጉ ተነገረ
ዓለም አቀፍ የሊቲየም ዋጋ በቀነሰበት ሁኔታ የዚምባብዌ የሊቲየም የወጪ ንግድ በ30 በመቶ ማደጉ ተነገረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.07.2025
ሰብስክራይብ

ዓለም አቀፍ የሊቲየም ዋጋ በቀነሰበት ሁኔታ የዚምባብዌ የሊቲየም የወጪ ንግድ በ30 በመቶ ማደጉ ተነገረ

በ2025 መጀመሪያ የዚምባብዌ የስፖዱሜን ክምችት ምርት የወጪ ንግድ 30 በመቶ አድጓል፡፡ ለውጭ የተላከው ምርት ባለፈው ዓመት ከነበረው 451 ሺህ 824 ቶን በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር 586 ሺህ 197 ቶን መድረሱን የምዕራባውያን የዜና ምንጭ የዚምባብዌ የማዕድን ግብይት ኮርፖሬሽንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

ከ2023 ጀምሮ በገበያ ላይ የተትረፈረፈ አቅርቦት በመኖሩ ምክንያት የሊቲየም ዋጋ በ90 በመቶ ገደማ ባሽቆለቆለበት ጊዜ የተሰተዋለ ጭማሪ ነው፡፡

ኋዩ ኮባልት እና ሳይኖማይን ጨምሮ የቻይና ኩባንያዎች የዚምባብዌን የሊቲየም ዘርፍ ተቆጣጥረውታል፡፡ ከ2021 ጀምሮ ከ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ መዋዕለ ነዋይ ፈሰስ ኣድርገዋል፡፡ አንዳንዶቹ የዚምባብዌን የ2027 ጥሬ እቃ ኤክስፖርት እገዳ ተከትሎ የሊቲየም ሰልፌት ፋብሪካዎችን እዚያው እየገነቡ ነው፡፡

የዚምባብዌ የማዕድን ግብይት ኮርፖሬሽን በታዳሽ ኃይል እና በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ዘርፎች የሚመራው ዓለም አቀፍ ፍላጎት በመቀጠሉ በመካከለኛ ጊዜ የገበያ ማገገም እንደሚኖር ይጠብቃል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0