ላቭሮቭ ከሞዛምቢክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያ ማኑኤላ ሳንቶስ ሉካስ ጋር የሰጡት መግለጫ
ላቭሮቭ ከሞዛምቢክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያ ማኑኤላ ሳንቶስ ሉካስ ጋር የሰጡት መግለጫ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፦
ሩሲያን በተመለከተ ምዕራባውያን ስለያዙት አቋም፦
◻ አውሮፓ "ብስጭቷ እያየለ" እና ሩሲያ ላይ የተከፈተ "የዓለም አቀፍ ግትርነት" ዘመቻ አካል ሆናለች፡፡
◻ ኪዬቭ የሽብር ተግባር እንድትፈጽም ለማነሳሳት የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ ተገቢውን የአጸፋ ምላሽ ያገኛል። ሞስኮ ሁሉንም ግቦቿን ታሳካለች፡፡
◻ ጀርመን ሰሞኑ ሩሲያ ላይ የሰነዘረችው ዛቻ ለማንኛውም አስተዋይ ሰው እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡
◻ የታሪክ ትምህርቶች መረሳት የለባቸውም፤ ነገር ግን የጀርመን እና የፈረንሳይ የዛሬ ትውልዶች በወጉ ትምህርት አልወሰዱም፡፡
በሩሲያ-ሞዛምቢክ እንዲሁም የአፍሪካ ግንኙነት በተመለከተ፦
ቀጣዩ የሞዛምቢክ-ሩሲያ የበይነ ምንግሥታት ኮሚሽን ስብሰባ በ2026 በማፑቶ ይካሄዳል፡፡
ሩሲያ ከፀረ ሽብር እና ከብሔራዊ መከላከያ አቅም ጋር በተያያዘ በሞዛምቢክ የተጠየቁ ድጋፎችን ሁሉ ለማገዝ ዝግጁ ናት፡፡
በተባበሩት መንግሥታት ውይይቶች ወቅት ሞዛምቢክ ስለ ዩክሬን ለምትይዘው ገለልተኛ አቋም ሩሲያ ዋጋ ትሰጣለች፡፡
ሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ የሚኒስትሮች ጉባኤ በዓመቱ መጨረሻ በግብጽ ይካሄዳል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X