የሩሲያ ጦር በዶኔስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ በኖቮቶሬትስኮይ የሚገኝ ይዞታን ነጻ እንዳወጣ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ
16:26 22.07.2025 (የተሻሻለ: 16:34 22.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ ጦር በዶኔስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ በኖቮቶሬትስኮይ የሚገኝ ይዞታን ነጻ እንዳወጣ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ጦር በዶኔስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ በኖቮቶሬትስኮይ የሚገኝ ይዞታን ነጻ እንዳወጣ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ
የሩሲያ ጦር በዶኔስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ትራቭንያ፣ ክራስኖአርሜይስክ፣ ፔትሮቭስኮዬ፣ ኡዳችኖዬ እና ፖልታቭካ እንዲሁም በዲኔፕሮፔትሮቭስክ ክልል ፊሊያ አካባቢዎች የተሰለፉ የዩክሬን ኃይል ብርጌዶችን ድል እንዳደረገ መከላከያ ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል፡፡
የሩሲያ ዘመቻ-ታክቲካል አቪዬሽን፣ የጥቃት ድሮኖች፣ የሚሳኤል ጦር እና መድፈኞች በግንባሩ 143 ቦታዎችን በማጥቃት፤ የዩክሬን ድሮን ማከማቻ መጋዘኖችን፣ የመገጣጠሚያ ቦታዎችን፣ የሰው አልባ አውሮፕላን አብራሪ ማሠልጠኛዎችን እንዲሁም የዩክሬን ጦር ክፍሎች፣ ብሔረተኞች እና የውጭ ቅጥረኞች ጊዜያዊ መገኛዎችን መምታቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
የሩሲያ የአየር መከላከያ ኃይሎችም ሁለት የዩክሬን ረጅም ርቀት "ኔፕቱን" ሚሳኤሎችን እና 259 ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች)ን መትተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X