ኢትዮጵያ ብሔራዊ የሆርቲካልቸር ስትራቴጂ እና የእንሰት ልማት ፕሮግራም ይፋ አደረገች
16:17 22.07.2025 (የተሻሻለ: 16:24 22.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ብሔራዊ የሆርቲካልቸር ስትራቴጂ እና የእንሰት ልማት ፕሮግራም ይፋ አደረገች
የኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር የእንሰት ተክል ከምግብነት ባለፈ ለገቢ ምንጭነት የሚውልባቸውን አማራጮች ለማስፋት ትኩረት መሰጠቱን ገልጿል። የሆርቲካልቸር ዘርፉን ምርታማነት ይበልጥ ለማሳደግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየተሠራ ነውም ብሏል።
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ "እነዚህ ፕሮግራሞች የተሳሰሩ ጥቅሞችን፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ የተሻሻለ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን፣ የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች መተካትን እና የተሻሻለ የወጪ ንግድ አቅምን ይሰጣሉ" ያሉ ሲሆን ገበሬዎች፣ ባለሀብቶች እና የልማት አጋሮች በሀገር አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ለመፍጠር እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በ2016/17 በጀት ዓመት ብቻ ኢትዮጵያ 286 ሺህ ቶን የሆርቲካልቸር ምርቶችን ልካ 565 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ አስገብታለች ተብሏል፡፡
ሀገሪቱ ከ25 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ለምግብነት ከሚጠቀሙት እንሰት ባለፈው ዓመት 3.6 ሚሊየን ዶላር የወጪ ንግድ ገቢ እንዳገኘች የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X