የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ሀብቶቿን በማቀናጀት የልማት ዕቅዶቿን ማሳካት እንደምትችል አሳይቷል ሲሉ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተናገሩ
15:48 22.07.2025 (የተሻሻለ: 15:54 22.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ሀብቶቿን በማቀናጀት የልማት ዕቅዶቿን ማሳካት እንደምትችል አሳይቷል ሲሉ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተናገሩ
የግድቡ ግንባታ ሀገሪቱ መከተል ያለባትን የልማት አቅጣጫ የጠቆመ እንደሆነ፤ ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ በተያዘው በጀት ዓመት የተከናወኑ ጉዳዮችን በተመለከተ ከተሰጠው መግለጫ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ቃለመጠይቅ የሰጡት ዋና ሥራ አስፈፃሚው አረጋዊ በርሄ [ዶ/ር] ተናግረዋል፡፡
"የሕዳሴ ግድብ ተርባይኖች የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ተጠምደዋል" ያሉት ኃላፊው፤ የግድቡ ግንባታ ወደ መጠናቀቁ መቃረቡን እና ምረቃውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ ባደረጉት መሠረት በመስከረም ወር መጨረሻ እንደሚጠበቅ አንስተዋል።
"እኛ ራሳችንን ከውጭ ለጋሾች እና አማካሪዎች ጋር አቆራኝተን ነው የኖርነው፤ ይህም ከውጭ ሀገራት በብድር አሊያም በእርዳታ መልክ የሚፈስ ነበር። ያ ለእኛ አልሰራልንም። ብቸኛው መንገድ የሕዝቡ አንድነት እና ችግሮቻችንን በራሳችን አቅም ለመፍታት ያለን ቁርጠኝነት ነው። በራሳችን ዕውቀት፣ በራሳችን የተፈጥሮ ሃብት እና በራሳችን የሰው ኃይል መልማት እንችላለን" ብለዋል።
ኃላፊው ከግድቡ ጋር ተያይዞ ከየትኛውም አካል የቅኝ ግዛት እሳቤን ሀገሪቱ ላይ ለመጫን የሚደረግ ሙከራን ኢትዮጵያውያን በተለመደ ያለመገዛት ታሪካቸው እንደሚታገሉትም አመላክተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X