ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሀገር በቀል ክሬዲት ካርድ አስጀመረች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሀገር በቀል ክሬዲት ካርድ አስጀመረች
ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሀገር በቀል ክሬዲት ካርድ አስጀመረች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.07.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሀገር በቀል ክሬዲት ካርድ አስጀመረች

የክፍያ ሥርዓቱ መሠረቱን የተባበሩት የአረብ ኢምሬቶች ባደረገው ሳኑፔይ እና በቤልጀሙ የሶፍትዌር ኩባንያ ኦፕንዌይ ትብብር እውን ሆኗል፡፡

"በኢትዮጵያ ምርጥ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለማቅረብ ምርጡን መፍትሄ መርጠናል፡፡ ከኦፕንፔይ ጋር የተፈጠረው ትብብር እና በዌይ4 ጠንካራ፣ የሚያድግ እና የተሳለጠ ሶፍትዌር መሠረተ ልማት የአፍሪካን ዲጂታል የፋይናንስ ሽግግር ይደግፋል" ሲሉ የሳኑፔ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አልፍሬድ ጋቻጋ ተናግረዋል፡፡

በኦፕንዌይ ዌይ4 ሶፍትዌር የሚሠራውን ክሬዲት ካርድ ባንኮች የሀገር ውስጥ የባንክ ደብተር ለያዙ ደንበኞች መስጠት እንደሚችሉ እና ከባንኮች፣ ከኤቲኤሞች እና ከፖስ ማሽኖች ጋር የተዋሃደ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

በዚህም መሠረት፦

ሳኑፔይ 4 ሚሊዮን የእዳ/ቅድመ ክፍያ ካርዶችን፣

5 ሺህ ቪዛ/ማስተርካርድ ክሬዲት ካርዶችን፣

10 ሺህ የፖስ ማሽን አገልግሎት መስጫዎችን እና

200 ኤቲኤም ማሽኖችን በአገልግሎት ላይ ያውላል፡፡

ኦሮሚያ ባንክ የመጀመሪያዎቹን የሀገር ውስጥ ክሬዲት ካርዶች ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መሠረተ ልማቱን የብሔራዊ ባንክ ፈቃድ አግኝቶ በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሰው ሳንቲምፔይ እንደሚደገፈው ተገልጿል፡፡ ድርጅቱ በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያውን የፖስ ማሽን መገጣጠሚያ ፋብሪካ መመረቁ የሚታወስ ነው፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0