ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከኤም23 ቡድን ጋር የደረሠችውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ በቅርቡ ሰላም እንደምታገኝ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከኤም23 ቡድን ጋር የደረሠችውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ በቅርቡ ሰላም እንደምታገኝ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናገሩ
ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከኤም23 ቡድን ጋር የደረሠችውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ በቅርቡ ሰላም እንደምታገኝ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.07.2025
ሰብስክራይብ

ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከኤም23 ቡድን ጋር የደረሠችውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ በቅርቡ ሰላም እንደምታገኝ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናገሩ

ጃክሜን ሻባኒ “የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና የኤም23 ቡድን ተወካዮች በስምንት ቀናት ወስጥ ወደ ዶሃ ይመለሳሉ፡፡ ሁሉም ነገር በጥሩ ሁኔታ ከቀጠለ በመጪዎቹ ወራት የሰላም ስምምነት ሊፈረም ይችላል” ሲሉ የዶሃ መርሆዎች ስምምነትን አስመለክቶ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

ኮንጎ እና የኤም23 ቡድን ባለፈው ቅዳሜ በኳታር ዶሃ የመርሆዎች ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱ ከሦስት ወር ንግግር በኋላ ዘላቂ የተኩስ አቁምን ያካትታል።

የዶሃው ድርድር በመጋቢት ወር በፕሬዝዳንት ሺሴኬዲ እና በፕሬዝዳንት ካጋሜ መካከል የተደረገውን ውይይት እና ሚያዚያ ወር ላይ የወጣውን የኮንጎ እና ኤም 23 የጋራ የተኩስ አቁም መግለጫ ተከትሎ የመጣ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

አዲሱ የመርሆዎች ስምምነት ሁለቱም ወገኖች ለሰላም ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያረጋግጡ ረድቷቸዋል፣ ሆኖም በፍጥነት መተማመንን መገንባት አስቸጋሪ ስለሆነ፤ አሸማጋዮች እነዚህን መርሆዎች በቅርቡ ለሚፈረመው የላቀ የሰላም ስምምነት ቁልፍ መመሪያዎች ለማድረግ መወሰናቸውን ባለሥልጣኑ ገልጸዋል፡፡

የመንግሥት ቃል አቀባይ ፓትሪክ ሙያያ "የተረጋገጠና ዘላቂ ሰላም እንፈልጋለን" ሲሉ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ተናግረዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0