ኢትዮጵያ በቅርቡ ይፋ የምታደረገው የአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ብሔራዊ ትግበራ ስትራቴጂ በማዕቀፉ ሥር መገበያየት ለመጀመር ቁልፍ እርምጃ እንደሆነ ባለሙያው ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በቅርቡ ይፋ የምታደረገው የአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ብሔራዊ ትግበራ ስትራቴጂ በማዕቀፉ ሥር መገበያየት ለመጀመር ቁልፍ እርምጃ እንደሆነ ባለሙያው ተናገሩ
ኢትዮጵያ በቅርቡ ይፋ የምታደረገው የአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ብሔራዊ ትግበራ ስትራቴጂ በማዕቀፉ ሥር መገበያየት ለመጀመር ቁልፍ እርምጃ እንደሆነ ባለሙያው ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.07.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በቅርቡ ይፋ የምታደረገው የአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ብሔራዊ ትግበራ ስትራቴጂ በማዕቀፉ ሥር መገበያየት ለመጀመር ቁልፍ እርምጃ እንደሆነ ባለሙያው ተናገሩ

ኢትዮጵያ በግንቦት ወር በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀውን የሸቀጦች አቅርቦት እና የቀረጥ ቅናሽ መርሃ ግብር ጨምሮ ቁልፍ ዝግጅቶችን አጠናቅቃለች፡፡

በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን፣ በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዲሁም በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ትብብር የተዘጋጀው የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የትግበራ ብሔራዊ ስትራቴጂ ባለፈው ወር ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ተመራማሪ እና የስትራቴጂ ዝግጅት የቴክኒክ ቡድን መሪ አበበ አምባቸው [ዶ/ር] “ኢትዮጵያ ይህንን እንደ ዕድል ትመለከተዋለች፤ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማስፋትና ከአኅጉሪቱ ቀሪ ክፍል ጋር እንድትዋሃድ ይረዳታል” ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

ባለሙያው አክለውም የሀገሪቱ የንግድ ምህዳር ከእድሉ በአግባቡ ለመጠቅም በቂ ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

“ግንዛቤ እጅግ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ የንግድ ዝግጁነትም ሌላኛው ጉዳይ ነው፤ ምክንያቱም መስፈርቶችን፣ ሕጎችን፣ ደንቦችን ማዋሃድ እና ከአኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ግዴታዎች እና ስምምነቶች ጋር ማጣጣም ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ሁሉንም ስትራቲጂዎች ነድፈናል” ብለዋል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ስትራቴጂውን ከቀረጥ አቅርቦቱ ሕትመት ጎን ለጎን በዚህ ወር ይፋ ያደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው ተመራማሪው የገለፁት፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0