ኬንያ የአክቲቪስት ቦኒፌስ ምዋንጊን የሽብር ክስ በማቋረጥ፤ ሕገ-ወጥ ጥይት በመያዝ ከሰሰችው
19:56 21.07.2025 (የተሻሻለ: 20:04 21.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኬንያ የአክቲቪስት ቦኒፌስ ምዋንጊን የሽብር ክስ በማቋረጥ፤ ሕገ-ወጥ ጥይት በመያዝ ከሰሰችው

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኬንያ የአክቲቪስት ቦኒፌስ ምዋንጊን የሽብር ክስ በማቋረጥ፤ ሕገ-ወጥ ጥይት በመያዝ ከሰሰችው
ባለሥልጣናት በበርካታ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ የክስ መዘገቦችን መክፈታቸውን ተከትሎ ሕዝባዊ ትችት ካስተናገስዱ በኋላ የመጣ ነው፡፡
ምዋንጊ የሀገሪቱ የወንጀል ምርመራ ዳይሪከቶሬት “የሽብር ተግባር በማቀነባበር” ቅዳሜ ያሠረበትን ክስ አስተባብሏል።
በናይሮቢ ፍርድ ቤት የቀረበው ምዋንጊ "ሕጋዊ ሥልጣን ሳይኖረው ሦስት አስለቃሽ ጭስ ተተኳሽ ጎጂ ንጥረ ነገሮችን" እንዲሁም የርችት ጥይት ይዞ በመገኘት ተከስሷል፡፡ ጥፋተኛ አለመሆኑን ተከራክሮ በአንድ ሚሊየን ሽልንግ (ወደ 7 ሺህ ዶላር) ዋስ ተለቅቋል፡፡
የአክቲቪስቱ እስር መንግሥት ላይ ያነጣጠሩ ተከታታይ ተቃውሞዎች እየተካሄዱ ባለበት ወቀት የመጣ ነው፡፡ ምዋንጊ ከዚህ ቀደምም ለእስር የተዳረገ ሲሆን ከሰሞኑ ደግሞ በታንዛኒያ ታስሮ በነበረበት ወቅት ደርሶብኛል ባለው በደል ዙሪያ በኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ መንግሥታት ላይ ክስ አቅርቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X