የሳሕል ሀገራት ጥምረት ከምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ እና የገንዘብ ሕብረት ‘አንገታቸውን ቀና አድርገው’ መውጣት አለባቸው - ባለሙያ
19:42 21.07.2025 (የተሻሻለ: 19:44 21.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሳሕል ሀገራት ጥምረት ከምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ እና የገንዘብ ሕብረት ‘አንገታቸውን ቀና አድርገው’ መውጣት አለባቸው - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሳሕል ሀገራት ጥምረት ከምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ እና የገንዘብ ሕብረት ‘አንገታቸውን ቀና አድርገው’ መውጣት አለባቸው - ባለሙያ
ኢሱፉ ቡባካር ካዶ ማጋጊ እንደሚሉት አሁን ባለው ሁኔታ ለኒጀር፣ ማሊ እና ቡርኪና ፋሶ ብቸኛው ወሳኔ ነው፡፡
ሦስቱ ሀገራት ለኦጋድጉ በሚገባው የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ እና የገንዘብ ሕብረት ተዘዋዋሪ ፕሬዝዳንትነት ተራ ዙሪያ አለመግባባት በመፈጠሩ ሐምሌ ወር መጀመሪያ ስብሰባ ረግጠው ወጥተዋል፡፡
"የሳሕል ሀገራት ጥምረት የፖለቲካ መሪዎች፣ በዓለም ኃያላን በሚመራ እና ከእነሱ በተቃርኖ በቆም የኢኮኖሚ ውህደት ድርጅት ውስጥ መቆየት በጣም አስቸጋሪ እንደሚሆን መገንዘብ አለባቸው" ሲሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡
ባለሙያው የገንዘብ ሉዓላዊነት "ለኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ልማት ቅድመ ሁኔታ" መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የሳሕል ሀገራት ጥምረት ተቋማዊ አቅም፦
የሳሕል ሀገራት ጥምረት 79 በመቶ የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ እና የገንዘብ ሕብረት ግዛትን እና 60 በመቶ የሕዝብ ቁጥር ይይዛሉ፣
በአጠቃላይ የእድገት ምጣኔ ደረጃ ኒጀር የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ እና የገንዘብ ሕብረት አባል ሀገራትን ትመራለች፡፡
"በምዕራብ አፍሪካ የፈረንሳይ ጥቅም አስጠባቂዋ" ኮትዲቯር "ለምዕራብ አፍሪካ እና የሳሕል የኢኮኖሚ ጥቅም ከባደ አደጋ ትጥላለች" ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X