የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 135.3 ሚሊየን መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት የሥነ-ሕዝብ ፈንድ የ2025 ሪፖርት ይፋ አደረገ
18:36 21.07.2025 (የተሻሻለ: 18:44 21.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 135.3 ሚሊየን መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት የሥነ-ሕዝብ ፈንድ የ2025 ሪፖርት ይፋ አደረገ
"ኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትን የሚያቀጣጠል እና አኗኗርን የሚያሻሽል የሥነ-ሕዝብ ዕድል አላት" ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የሥነ-ሕዝብ ፈንድ ምክትል ተወካይ ታይዎ ኦሉዮሚ ሪፖርቱ ይፋ ሲደረግ ተናግረዋል፡፡
የተቋሙ ሪፖርት፦
🟠 የውልደት ምጣኔ በ2025 በአንድ እናት 3.81 ህጻናት፤
🟠 ከተሜነት 22.5 በመቶ እንደሆነም አስቀምጧል፡፡
ትንበያው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር በ2035 ከ170 ሚሊየን በላይ፤ በ2050 ወደ 225 ሚሊየን ሊጠጋ ይችላል ብሏል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X