መከረኛዋ ጋዛ፤ አዳዲስ መረጃዎች
◻ የኔትዛሪም ክስተት፦ በጋዛ ከተማ ደቡብ እርዳታ ሲጠብቁ በነበሩ ሁለት ሰዎች በእስራኤል ኃይሎች መገደላቸውን ፍልስጤማውያን ምንጮች ገልፀዋል፡፡
◻ የአየር ድብደባ መባባስ፦ በሰርጡ በተፈፀመው የእስራኤል ጥቃት 17 ሰዎች መሞታቸውን የጋዛ ሆስፒታሎች ዛሬ ጠዋት አስታውቀዋል፡፡
◻ የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ ማስጠንቀቂያ፦ ኤጀንሲው እገዳው እንዲቆም እና ለሰብዓዊ እርዳታ አስቸኳይ ደህንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያ እንዲፈጠር ጠይቋል፡፡
◻ የምድር ዘመቻዎች መስፋፋት፦ የእስራኤል ኃይሎች በማዕከላዊ ጋዛ በምትገኘው ዴር አል-ባላህ ጥቃት እያካሄዱ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X