የኢትዮጵያ መንግሥት አይኤምኤፍ ብሔራዊ ባንክ በገለልተኛ ባለሙያዎች እንዲመራ ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ውድቅ አደረገ
16:40 21.07.2025 (የተሻሻለ: 19:24 21.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ መንግሥት አይኤምኤፍ ብሔራዊ ባንክ በገለልተኛ ባለሙያዎች እንዲመራ ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ውድቅ አደረገ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ መንግሥት አይኤምኤፍ ብሔራዊ ባንክ በገለልተኛ ባለሙያዎች እንዲመራ ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ውድቅ አደረገ
የዓለም የገንዘብ ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግሥት የኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራም ጋር በተያያዘ የባንኩን ተቋማዊ ነጻነት ለማረጋገጥ ገዥው፣ ምክትላቸው እና የባንኩ የቦርድ አመራሮች ገለልተኛ እንዲሆኑ በ2017 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ሃሳቡን አቅርቦ እንደነበር የሀገር ውስጥ ጋዜጣ ነው የዘገበው፡፡
ሆኖም የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ሕገ-መንግሥቱን ይቃረናል በማለት እንዳልተቀበሉት አይኤምኤፍ ገልጿል፡፡
አበዳሪው በተሻሻለው አዲሱ የብሔራዊ ባንክ አዋጅ መሠረት በቀጣዮቹ ወራት ሦስት ገለልተኛ የቦርድ አመራሮች ሊመደቡ እንደሚገባ አሳስቧልም ነው የተባለው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X