ሩሲያ እና ዩክሬን በዚህ ሳምንት ኢስታንቡል ውስጥ አዲስ ድርድር ሊያካሂዱ ይችላሉ ተባለ
13:39 21.07.2025 (የተሻሻለ: 14:24 21.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ዩክሬን በዚህ ሳምንት ኢስታንቡል ውስጥ አዲስ ድርድር ሊያካሂዱ ይችላሉ ተባለ
ድርድሩ እሮብ ወይም ሐሙስ ሊካሄድ እንደሚችል የዲፕሎማሲ ምንጮች ለቱርክ ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡ ስለ ጊዜ፣ ቦታ እና ልዑካን ቡድኑ ስብጥር የተለየ መረጃ አልተገለጸም።
ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የዩክሬን ብሄራዊ ደህንነት እና መከላከያ ምክር ቤት ፀሀፊ ረስተም ኡሜሮቭ በሚቀጥለው ሳምንት ከሩሲያ ጋር አዲስ ስብሰባ ለማድረግ ሀሳብ ማቅረባቸውን ቅዳሜ አስታውቋል።
የሩሲያ የልዑካን ቡድን ምንጭ ሀሳቡን ለስፑትኒክ አረጋግጧል። ተጨማሪ የሞስኮ ምንጭ ከኪዬቭ የሚመጡ ምልክቶች የድርድር ተስፋ እንደሰጡ ተናግረዋል፡፡
ሩሲያ እና ዩክሬን ቀደም ሲል በኢስታንቡል ሁለት ዙር ቀጥተኛ ድርድር አድርገዋል። እነዚህ ድርድሮች የእስረኞች ልውውጥ እና የዩክሬን ወታደሮች አስከሬን እንዲመለሱ አስችለዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች ግጭቱን ለመፍታት የሚያስችል ረቂቅ የመግባቢያ ሰነድ መለዋወጣቸውም የሚታወስ ነው።