የጣና ሐይቅና በዙሪያው ያሉ ደሴቶች የዓለም ቅርስ ሆነው በዩኔስኮ ሊመዘገቡ ነው ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየጣና ሐይቅና በዙሪያው ያሉ ደሴቶች የዓለም ቅርስ ሆነው በዩኔስኮ ሊመዘገቡ ነው ተባለ
የጣና ሐይቅና በዙሪያው ያሉ ደሴቶች የዓለም ቅርስ ሆነው በዩኔስኮ ሊመዘገቡ ነው ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.07.2025
ሰብስክራይብ

የጣና ሐይቅና በዙሪያው ያሉ ደሴቶች የዓለም ቅርስ ሆነው በዩኔስኮ ሊመዘገቡ ነው ተባለ

የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በጣና ሐይቅ ዙሪያ ያሉ ደሴቶችን ጨምሮ በ3600 ኪ.ሜትር ስፋት ርቀት ያለውን የሐይቁን አካባቢ በተፈጥሮዓዊና በባሕላዊ የዓለም ቅርስ ዝርዝር ውስጥ እንደሚመዘግብ ተገልጿል፡፡

“ላለፉት ሁለት ዓመታት ሐይቁን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ሰፊ ሥራ ሲሰራ ቆይቷል። በቅርቡም ተቀባይነት ማግኘቱን ከድርጅቱ ለቢሮው የኢሜል መልዕክት ተልኳል” ሲሉ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አየለ አናውጤ (ዶ/ር) ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

ዩኔስኮ ሁለቱንም (ተፈጥሮዓዊና ባሕላዊ) የያዘ ቅርስ ሲመዘግብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል ነው የተባለው፡፡ ውሳኔው በሚቀጥለው ዓመት ጥር ወር ላይ ዩኔስኮ በሚያካሂደው 48ኛ ጉባኤ ላይ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል፡፡

በጣና ሐይቅ ከሚገኙት በቋጥኝ እና በደን የተሸፈኑ ከ37 በላይ ደሴቶች 19ኙ ታሪካዊ ገዳማትን እና አድባራትን ይዘዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0