ፓሺንያን የአርሜንያ ቤተ-ክርስቲያን መሪን ለማበረር ዛቱ
19:27 20.07.2025 (የተሻሻለ: 19:44 20.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፓሺንያን የአርሜንያ ቤተ-ክርስቲያን መሪን ለማበረር ዛቱ
የአርሜኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያን ካቶሊኮስ ጋሬጊን 2ኛን ከታሪካዊው የኢችሚአዚን መኖሪያ ቤት ለማባረር መዘጋጀታቸውን በማስጠንቀቅ ደጋፊዎቻቸው “እንዲዘጋጁ” ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ቤተ-ክርስቲያን እና መንግሥት ቢለያዩም ፓሺንያን እርምጃውን የወሰዱት እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ብቻ ሳይሆን እንደ አማኝም ነው ብለዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ እርምጃ ቤተ-ክርስቲያኗ ላይ ከተካሄደው ጥቃት እና በሁለቱ የፓሺንያን ተቺዎች ማለትም የነጋዴው ሳምቬል ካራፔትያን እንዲሁም የሊቀ ጳጳስ ሚካኤል አድጃፓህያን እስርን ተከትሎ የመጣ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X