ዚምባብዌ ሕገ-ወጥ የውሃ አቅራቢ ነጋዴዎች ላይ ዘመቻ ጀመረች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዚምባብዌ ሕገ-ወጥ የውሃ አቅራቢ ነጋዴዎች ላይ ዘመቻ ጀመረች
ዚምባብዌ ሕገ-ወጥ የውሃ አቅራቢ ነጋዴዎች ላይ ዘመቻ ጀመረች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.07.2025
ሰብስክራይብ

ዚምባብዌ ሕገ-ወጥ የውሃ አቅራቢ ነጋዴዎች ላይ ዘመቻ ጀመረች

የዚምባብዌ ብሔራዊ የውሃ ባለሥልጣን ሀገር አቀፍ ዘመቻው የውሃ አቅርቦት ዘርፉን ለመቆጣጠር እና የኅብረተሰብ ጤና ለመጠበቅ ያለመ ነው ብሏል፡፡

ዘመቻው በከተማ አካባቢዎች ቁጥጥር ያልተደረገበትን የውሃ ማውጣት እና አቅርቦት በተመለከተ የቀረቡ የሕዝብ ቅሬታዎችን የሚመለስ መሆኑ ተነገሯል፡፡ ባለሥልጣናት ያለተጣራ ውሃ ንግድ የጤና አደጋ እንደሚያስከትል እና ብሔራዊ ደንቦችን እንደሚጥስ ይናገራሉ፡፡

የባለሥልጣኑ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን እና ግብይት ኃላፊ ማርጆሪ ሙንዮንጋ፤ ዘመቻው የጉድጓድ ቆፋሪዎች እና የውሃ አቅርቦት የጭነት መኪናዎችን ጨምሮ ሁሉም ያለተጣራ ውሃ ነጋዴዎች እንዲመዘገቡ ከሚያስገድደው ሕግ ጋር የተጣጣመ ነው ሲሉ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

የተለየ ፈቃድ ሳይኖር ከመኖሪያ አካባቢዎች ውሃ ማውጣት ሕገ-ወጥ ነው ያሉት ሙንዮንጋ፤ ተቋማቸው ለጥራት ቁጥጥር የውሃ ናሙናዎችን የመሰብሰብ ሥልጣን እንዳለው እና ከአቅራቢዎች ትክክለኛ የውሃ መገኛ ምዝገባን እንደሚጠይቅም ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0