ከ45 በላይ የሀገራት መሪዎች በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ እንደሚገኙ ይጠበቃል

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከ45 በላይ የሀገራት መሪዎች በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ እንደሚገኙ ይጠበቃል
ከ45 በላይ የሀገራት መሪዎች በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ እንደሚገኙ ይጠበቃል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.07.2025
ሰብስክራይብ

ከ45 በላይ የሀገራት መሪዎች በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ እንደሚገኙ ይጠበቃል

ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በወሳኝ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ድርድሮች ላይ አፍሪካ ቅድሚያ የምተሰጣቸውን ጉዳዮች ወደፊት ያመጣል ያሉትን ጉባኤ ለማሳካት ጥረት እያደረጉ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ፦

ከ45 በላይ የሀገራት መሪዎች እንደሚገኙ፣

ከ45 በላይ ጉባኤ ተኮር ይፋዊ ሁነቶች፣ 

ከ100 በላይ የጎንዮሽ ሁነቶች፣

ከ20 በላይ ከአፍሪካ ኅብረት አባል ሀገራት፣ የተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎች፣ የልማት አጋሮች እና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት ጋር መደበኛ ምክክሮች እንደሚካሄዱ ገልጸዋል።

የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አስፋ “አፍሪካ ቅድሚያ የምትሰጣቸውን ጉዳዮቿን የሚያንፀባርቅ እና እውነተኛ ውጤቶችን የሚያመጣ መድረክ ያስፈልጋታል። ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ያ መድረክ ነው። ድምጾችን ወደ አንድ ያመጣል፣ አሰላለፍንና ጥምረቶችን ይገነባል እንዲሁም ውጥናችን በራሳችን መንገድ ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችል እድል ይፈጥራል” ብለዋል፡፡

ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ “የዓለም የአየር ንብረት መፍትሄዎችን ማቀላጠፍ፤ የአፍሪካን ዘላቂ እና አረንጓዴ ልማት በገንዘብ መደገፍ” በሚል መሪ ቃል ከጳጉሜ 3-5 በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0