የአሜሪካ ቀረጥ ደቡብ አፍሪካ ወደ ብሪክስ ገበያዎች የምታደርገውን ሽግግር ሊያፋጥነው ይችላል ሲሉ ምሁሩ ገለጹ
11:10 19.07.2025 (የተሻሻለ: 11:14 19.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአሜሪካ ቀረጥ ደቡብ አፍሪካ ወደ ብሪክስ ገበያዎች የምታደርገውን ሽግግር ሊያፋጥነው ይችላል ሲሉ ምሁሩ ገለጹ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአሜሪካ ቀረጥ ደቡብ አፍሪካ ወደ ብሪክስ ገበያዎች የምታደርገውን ሽግግር ሊያፋጥነው ይችላል ሲሉ ምሁሩ ገለጹ
ቀረጡ በአሜሪካ ሸማቾች ላይ የዋጋ ጭማሪ ሊያስከትል እና እንደ ማዕድንና ግብርና ባሉ የደቡብ አፍሪካ ቁልፍ የወጪ ንግድ ምርቶች ላይ ያለውን ፍላጎት እንዲቀንስ ያደርጋል ሲሉ የኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዝዌሌቱ ጆሎቤ አመልክተዋል።
ጆሎቤ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደተናገሩት ቀረጡ የደቡብ አፍሪካን ምርቶች "ተወዳዳሪነት" በማቀጨጭ የአሜሪካ ገበያ ድርሻቸውን ሊቀንስ ይችላል።
በግብርና እና ማዕድን ዘርፎች የአጭር ጊዜ ሥራ ማጣት ሊከሰት እንደሚችል ገልጸው፤ የአሜሪካ የወጪ ንግድ አስፈላጊነትን ከልክ በላይ ማጋነን እንዳማያስፈልግ ጠቁመዋል። ለዚህም ተገማች ያልሆነውን ግንኙነት በመጥቀስ፤ አሜሪካ "ብቸኛ" የወጪ ንግድ መዳረሻ እንዳልሆነች አብራርተዋል።
"አማራጩ በመጀመሪያ ደረጃ አዳዲስ ገበያዎችን መፈለግ ነው፤ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በብሪክስ ውስጥ ባሉ ነባር ገበያዎች ተጨማሪ ዕድሎችን ማግኘት ነው ብዬ አስባለሁ" ብለዋል።
የዩኤስኤአይዲ የገንዘብ ድጋፍ እና የወጪ ንግድ ገቢ መቀነስን በተመለከተ፤ የገቢ ተፅዕኖ ለማቅለል ደቡብ አፍሪካ የማህበራዊ ፕሮግራሞችን በተሻለ ውጤታማነት እና በዝቅተኛ ወጪ ማካሄድ እንደምትችል ተናግረዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X