የኬንያ ከቪዛ ነፃ ፖሊሲ የአፍሪካን ንግድና ቱሪዝም ያሳድጋል - ኬንያዊ የሕግ ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የኬንያ ከቪዛ ነፃ ፖሊሲ የአፍሪካን ንግድና ቱሪዝም ያሳድጋል - ኬንያዊ የሕግ ባለሙያ

ኬንያ አፍሪካውያን ተጓዦች ያለ ቪዛ እንዲገቡ መፍቀዷ አህጉር አቀፍ ንግድን ለማሳደግ እና በተለመዱ የውጭ ገበያዎች ላይ የነበረውን ጥገኝነት ለመቀነስ የሚረዳ ተራማጅ እርምጃ ነው ሲሉ የአፍሪካ የእርማትና ቅደመ መከላከል ማዕከል ጠበቃ ኬልቪን ሙጋምቢ ኩባይ ተናግረዋል።

"ይህ እርምጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ኬንያ የሚመጡ አፍሪካውያን እና የካሪቢያን ጎብኝዎች እንቅስቃሴን ይጨምራል። የቱሪዝም ፍሰቱንም ያሳድገዋል። ብቸኛው አሉታዊ ተጽዕኖ ከፀጥታ ጋር የተያያዘ ይሆናል፤ ምክንያቱም አንዳንድ ክፉ አላማ ያላቸው ጎብኚዎች ሊኖሩ ይችላሉ" ብለዋል።

አክለውም አዲሱ የኤሌክትሮኒክስ የጉዞ ፈቃድ ተሳፋሪዎች በበረራዎች መካከል ፈጣን የሳፋሪ ቆየታ በማድረግ ለ12 ሰዓታት ኬንያን እንዲጎበኙ ያስችላቸዋል።

ኩባይ ፓሊሲውን እንደ ጃማይካ፣ ባርቤዶስ እና  ባሃማስ ባሉ የካሪቢያን ሀገሮች ላይ ተግባራዊ መሆኑ እና ዓለም አቀፍ ይዘት እንዲኖረው መደረጉ፦

ባሕላዊ እና ታሪካዊ ትስስርን ለማጠናከር፤

የአፍሪካ ሀገራት በደቡባዊው ዓለም ያላቸውን የጋራ ጥንካሬ በመጠቀም በንግድ እና ልማት የበለጠ ትብብር እንዲያጎለብቱ ይረዳል ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0