የሩሲያ የመርከበኞች ማሠልጠኛ መርከብ ክሩዘንስቴርን የታላቁን የአፍሪካ የባሕር ጉዞ አጠናቀቀ
19:20 19.07.2025 (የተሻሻለ: 19:24 19.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ የመርከበኞች ማሠልጠኛ መርከብ ክሩዘንስቴርን የታላቁን የአፍሪካ የባሕር ጉዞ አጠናቀቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ የመርከበኞች ማሠልጠኛ መርከብ ክሩዘንስቴርን የታላቁን የአፍሪካ የባሕር ጉዞ አጠናቀቀ
መጋቢት 9 በጀመረው ጉዞ መርከቡ ባልቲክ እና የሰሜን ባሕርን አልፎ ወደ አትላንቲክ እና ህንድ ውቅያኖሶች ገበቷል።
መርከቡ ያረፈባቸው ወደቦች፦
አጋዲር፣
ካዛብላንካ፣
ኬፕ ታውን፣
ፖርት ሉዊስ።
መርከቡ በሞሪሺየስ በነበረው የተለየ ቆይታ እ.ኤ.አ በ1975 የሶቪየት የባሕር ኃይል ለደሴቲቱ ያደረገውን ድጋፍ እንዲሁም ናዚ ድል የተደረገበት 80ኛ ዓመት በዓል ተዘክሯል።
የጉዞው ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 በግምት 20 ሺህ ኖቲካል ማይል ተጉዟል፣
🟠 ከ15 ሺህ በላይ ኖቲካል ማይል ሸፍኗል፣
🟠 የምድር ወገብ እና የቀትር መስመርን ሁለት ጊዜ አቋርጧል፤
🟠 ከ80 በላይ የአደጋ ጊዜ ልምምዶችን አካሂዷል።
ከአምስት የሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ 140 ካዴቶች ከግብፅ፣ ሞሮኮ፣ ኩባ እና ካዛክስታን ከመጡ 13 የውጭ ሀገር ሠልጣኞች ጋር የመጀመሪያ የባሕር ሥልጠናቸውን አጠናቀዋል።
መርከቧን የሚያንቀሳቅሰው የካሊኒንግራድ ስቴት ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ አመራር እና የክሩዘንስቴርን መርከበኞች ጉዞው የተሳካ እንደሆነ ገልፀው፤ መርከቧ፣ ሠራተኞቿ እና ካዴቶች በውጭ ሀገር ወደቦች በቆዩበት ጊዜ ሩሲያን በሚያስደንቅ ሁኔታ ወክለዋል ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X