ለኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ጥበቃ አዲስ ተስፋ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱለኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ጥበቃ አዲስ ተስፋ
ለኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ጥበቃ አዲስ ተስፋ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.07.2025
ሰብስክራይብ

ለኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ጥበቃ አዲስ ተስፋ

ሀገሪቱ ለአዲሱ የዓለም ብዝሃ ሕይወት ማዕቀፍ ፈንድ የ16.8 ሚሊየን ዶላር ድርሻ ብቁ ከሆኑ ሀገራት ውስጥ ተካታለች።

ፈንዱ ከነሐሴ 25 ጀምሮ ክፍት ይሆናል። የኩሚንግ-ሞንትሪያል የብዝሃ ሕይወት ማዕቀፍ አካል የሆነው ይህ ፈንድ፤ በፈረንጆቹ 2023 በቫንኩቨር ካናዳ ይፋ የተደረገ ሲሆን በ186 ሀገራት ፀድቋል።

ማዕቀፉ በድሃ ሀገራት እና በማደግ ላይ ባሉ አነስተኛ የደሴት ሀገራት ለብዝሃ ሕይወት ጥበቃ የገንዘብ ድጋፍ ፈሰስ ለማድረግ የተቋቋመ ነው።

በ2024 ወደ ሥራ በገባው በፕሮግራሙ የመጀመሪያ ዙር ድጋፍ፤ በ41 ሀገራት ውስጥ ለሚካሄዱ 41 የአካባቢ ጥበቃ ፕሮጀክቶች 201.6 ሚሊየን ዶላር ተመድቧል። ኢትዮጵያ አሁን በሁለተኛው ዙር ድጋፍ ለማግኘት የፕሮጀክት ዝግጅቷን ማቅረብ ትችላለች ተብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0