የአፍሪካ ኅብረት በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኤም23 ያወጡትን የሰላም መግለጫ በደስታ ተቀበለ
17:28 19.07.2025 (የተሻሻለ: 18:14 19.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ ኅብረት በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኤም23 ያወጡትን የሰላም መግለጫ በደስታ ተቀበለ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ኅብረት በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኤም23 ያወጡትን የሰላም መግለጫ በደስታ ተቀበለ
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሐሙድ አሊ ዮሱፍ ስምምነቱን ለቀጣናው "ዘላቂ ሰላም እና ትብብር አዲስ ተስፋ የፈነጠቀ" ሲሉ አወድሰውታል።
በኳታር እና በአሜሪካ ሽምግልና የተደረሠው የመርህ ስምምነት ሁለቱ ወገኖች፦
አስቸኳይ የተኩስ አቁም፣
በ10 ቀናት ውስጥ ሁሉን አቀፍ የሰላም ስምምነት ላይ መድረስ የሚያስችል ቀጥተኛ ድርድር እንዲጀምሩ ያስቀምጣል።
🟠 የዶሃው ስምምነት ሰኔ 20 በዋሽንግተን የተፈረመውን የኮንጎ እና ሩዋንዳ የሰላም ስምምነት ተከትሎ የመጣ ነው። በቅርቡ በዋሽንግተን ይካሄዳል ተብሎ የታቀደው የመሪዎች ጉባኤ የሰላም ስምምነቱን ለማጠናቀቅ እና በአሜሪካ የሚደገፉ የጋራ የማዕድን ፕሮጀክቶችን ወደ ትግበራ ለማሸጋገር አልሟል።
ℹ የኮንጎ መንግሥት ሩዋንዳ የኤም23 አማፂያንን ትደግፋለች በማለት ሲከስ፤ ሩዋንዳ በበኩሏ ኮንጎን ግዛቷን የሚያጠቁ አማፂያንን በመሸሸግ ትወነጅላለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X