ኢትዮጵያ የትራምፕን ቀረጥ ተከትሎ አማራጭ የቡና ገበያዎችን እየቃኘሁ ነው አለች
15:26 19.07.2025 (የተሻሻለ: 15:34 19.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የትራምፕን ቀረጥ ተከትሎ አማራጭ የቡና ገበያዎችን እየቃኘሁ ነው አለች
የአሜሪካ አስተዳደር ፖሊሲ ከሀገሪቱ የወጪ ንግድ ገቢ 35 በመቶ የሚሆነውን የሚነካ በመሆኑ አማራጭ ገበያዎችን መመልከት ግድ ሆኗል ያሉት የቡናና ሻይ ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር ሻፊ ዑመር ናቸው።
የባለሥልጣኑ እቅድ፦
🟠 ወደ ሩቅ ምስራቅ እና መካከለኛው ምስራቅ የቡና ገበያ ማስፋት፣
🟠 በተያዘው በጀት ዓመት 20 አዳዲስ የቡና ወጪ ንግድ መዳረሻዎችን መክፈት፣
🟠 ቻይና፣ ጃፓን፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ጀርመን እና ጣሊያን ጋር ግኑኝነት ማጠናከርን ያካትታል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የቡና ዘርፉን የሚጎዳ የትኛውንም ዓይነት እርምጃ አይቀበልም ሲሉ ኃላፊው ለሺንዋ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X