ቻይና፣ ህንድና ሩሲያ ግዙፍ የኢንዱስትሪ ኢኮኖሚ ካላቸው ቀዳሚ አምስት ሀገራት ውስጥ ተቀመጡ
12:13 19.07.2025 (የተሻሻለ: 12:14 19.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቻይና፣ ህንድና ሩሲያ ግዙፍ የኢንዱስትሪ ኢኮኖሚ ካላቸው ቀዳሚ አምስት ሀገራት ውስጥ ተቀመጡ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቻይና፣ ህንድና ሩሲያ ግዙፍ የኢንዱስትሪ ኢኮኖሚ ካላቸው ቀዳሚ አምስት ሀገራት ውስጥ ተቀመጡ
ስፑትኒክ የዓለም ባንክን የ2024 መረጃ በመተንተን ባገኘው መረጃ መሠረት፦
🟠 ቻይና በዓለም ቀዳሚ የኢንዱስትሪ ኃያል ስትሆን ዘርፉ ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ በ2 በመቶ ገደማ በማደግ 6.8 ትሪሊየን ዶላር ደርሷል።
🟠 ህንድ በአራተኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ የኢንዱስትሪ ምርቷ በ4 በመቶ በማደግ 957 ቢሊየን ዶላር ደርሷል።
🟠 ሩሲያ ከአስሩ ታላላቅ ኢኮኖሚዎች መካከል ጠንካራውን ዕድገት አሳይታለች። የኢንዱስትሪ ዘርፉ ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያደረገው አስተዋፅኦ በ6 በመቶ አድጎ 668 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን በዚህም አምስተኛ ደረጃ ላይ እንድትቀመጥ አድርጓታል።
ዩናይትድ ስቴትስ እና ጀርመን በቅድመ ተከተል ሁለተኛ እና አራተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X