https://amh.sputniknews.africa
የዓባይ ግድብ ጉዳይ የአሜሪካ አደራዳሪነት የማያሻው፤ በሦስቱ ሀገራት ማለቅ ያለበት ነው ሲሉ ኢትዮጵያዊው የውኃ ሐብት ባለሙያ ተናገሩ
የዓባይ ግድብ ጉዳይ የአሜሪካ አደራዳሪነት የማያሻው፤ በሦስቱ ሀገራት ማለቅ ያለበት ነው ሲሉ ኢትዮጵያዊው የውኃ ሐብት ባለሙያ ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
የዓባይ ግድብ ጉዳይ የአሜሪካ አደራዳሪነት የማያሻው፤ በሦስቱ ሀገራት ማለቅ ያለበት ነው ሲሉ ኢትዮጵያዊው የውኃ ሐብት ባለሙያ ተናገሩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ በግድቡ ዙሪያ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ የግብፅ አቻቸው... 18.07.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-07-18T22:09+0300
2025-07-18T22:09+0300
2025-07-18T22:14+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07e9/07/12/998272_0:0:720:405_1920x0_80_0_0_9ab91eafa875197865855eb24594a214.jpg
የዓባይ ግድብ ጉዳይ የአሜሪካ አደራዳሪነት የማያሻው፤ በሦስቱ ሀገራት ማለቅ ያለበት ነው ሲሉ ኢትዮጵያዊው የውኃ ሐብት ባለሙያ ተናገሩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ በግድቡ ዙሪያ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ የግብፅ አቻቸው አብደል ፈታህ አል ሲሲ አድናቆታቸውን ገልፀዋል። የቀድሞው የዓባይ ግድብ ተደራዳሪ ፈቅአሕመድ ነጋሽ ግብፆች የአሜሪካን ተሳትፎ ለምን እንደፈለጉ እንደማይረዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። "ውሃው የሚፈሰው በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል ነው። እነሱ ናቸው ከውሃው ጋር በተፈጥሮ የተገናኙት። የሦስተኛ ወገኖች ተሳትፎ አይመከርም፤ ምክንያቱም ሦስተኛ ወገኖች የሀገራቱን ጥርጣሬ፣ ስጋት እና ፍላጎት አይረዱም። በተቃራኒው ሀገራቱ ራሳቸው ናቸው ይህን ሊያውቁ የሚችሉት" ብለዋል።ባለሙያው ሀገራቱ እርስ በርሳቸው በጉዳዩ ዙሪያ መነጋገር እንዲጀምሩ መክረዋል።"ሦስተኛ አካል ካስፈለጋቸውም ለሁሉም የጋራ የሆኑና ስጋት እና ፍላጎቶቻቸውን የሚረዱ እንደ አፍሪካ ኅብረት፣ የዓባይ ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ እና ሌሎች ተቋማትን ማሳተፉ ነው የሚሻለው። በዚህ ሰዓት ዩናይትድ ስቴትስን ማሳተፉ አስፈላጊ መስሎ አይታየኝም፤ ምክንያቱም ቀሪው ጉዳይ ዓመታዊው አስተዳደር ነው። ይህ ደግሞ በየዓመቱ የሚቀያየር ነው።" ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2025
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07e9/07/12/998272_90:0:630:405_1920x0_80_0_0_fc405f349930e9ef19e59fb3481cd075.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
የዓባይ ግድብ ጉዳይ የአሜሪካ አደራዳሪነት የማያሻው፤ በሦስቱ ሀገራት ማለቅ ያለበት ነው ሲሉ ኢትዮጵያዊው የውኃ ሐብት ባለሙያ ተናገሩ
22:09 18.07.2025 (የተሻሻለ: 22:14 18.07.2025) የዓባይ ግድብ ጉዳይ የአሜሪካ አደራዳሪነት የማያሻው፤ በሦስቱ ሀገራት ማለቅ ያለበት ነው ሲሉ ኢትዮጵያዊው የውኃ ሐብት ባለሙያ ተናገሩ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ በግድቡ ዙሪያ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ የግብፅ አቻቸው አብደል ፈታህ አል ሲሲ አድናቆታቸውን ገልፀዋል። የቀድሞው የዓባይ ግድብ ተደራዳሪ ፈቅአሕመድ ነጋሽ ግብፆች የአሜሪካን ተሳትፎ ለምን እንደፈለጉ እንደማይረዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"ውሃው የሚፈሰው በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል ነው። እነሱ ናቸው ከውሃው ጋር በተፈጥሮ የተገናኙት። የሦስተኛ ወገኖች ተሳትፎ አይመከርም፤ ምክንያቱም ሦስተኛ ወገኖች የሀገራቱን ጥርጣሬ፣ ስጋት እና ፍላጎት አይረዱም። በተቃራኒው ሀገራቱ ራሳቸው ናቸው ይህን ሊያውቁ የሚችሉት" ብለዋል።
ባለሙያው ሀገራቱ እርስ በርሳቸው በጉዳዩ ዙሪያ መነጋገር እንዲጀምሩ መክረዋል።
"ሦስተኛ አካል ካስፈለጋቸውም ለሁሉም የጋራ የሆኑና ስጋት እና ፍላጎቶቻቸውን የሚረዱ እንደ አፍሪካ ኅብረት፣ የዓባይ ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ እና ሌሎች ተቋማትን ማሳተፉ ነው የሚሻለው። በዚህ ሰዓት ዩናይትድ ስቴትስን ማሳተፉ አስፈላጊ መስሎ አይታየኝም፤ ምክንያቱም ቀሪው ጉዳይ ዓመታዊው አስተዳደር ነው። ይህ ደግሞ በየዓመቱ የሚቀያየር ነው።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X