የኢትዮጵያ መንግሥት በ2018 የበጀት ዓመት ለ5.6 ሚሊየን ዜጎች ሥራ ለመፍጠር ማቀዱን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ መንግሥት በ2018 የበጀት ዓመት ለ5
የኢትዮጵያ መንግሥት በ2018 የበጀት ዓመት ለ5 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.07.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ መንግሥት በ2018 የበጀት ዓመት ለ5.6 ሚሊየን ዜጎች ሥራ ለመፍጠር ማቀዱን አስታወቀ

ይህ የተገለፀው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2018 ሀገራዊ የልማት እቅድን በገመገመበት ወቅት ነው።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ ባቀረቡት ዕቅድ መሠረት መንግሥት፦

🟠 429 ሺህ 175 ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በመደገፍ ቁልፍ የሥራ እድል ፈጣሪዎች ለማድረግ፣

🟠 ለነዚህ ቢዝነሶች 48 ቢሊየን ብር ብድር ለማመቻቸት አቅዷል።

የውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪትን በተመለከተ፦

🟠 ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች የሚሠማሩባቸውን ሀገራት ከአምስት ወደ ስምንት ማሳደግ፣

🟠 ለ800 ሺህ ኢትዮጵያውያን በውጭ ሀገራት የሥራ ዕድሎችን መፍጠር የእቅዱ አካል ነው።

እቅዱ ዘላቂ እና ክብርን የጠበቁ ቅጥሮችን ከግምት ውስጥ ያስገባ እንደሆነም ተነግሯል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0