ኢትዮጵያ ከካርበን ሽያጭ 115 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት እየሠራች ነው ተባለ
19:52 18.07.2025 (የተሻሻለ: 19:54 18.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከካርበን ሽያጭ 115 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት እየሠራች ነው ተባለ
ሀገሪቱ ከአንድ ዓመት በፊት ከኖርዌይ መንግሥት ጋር የ75 ሚሊየን ዶላር የካርበን ሽያጭ ስምምነት ላይ ደርሳለች፡፡
በስምምነቱ መሠረት በመጀመሪያ እ.ኤ.አ ከ2018 እስከ 2022፤ በሁለተኛ ዙር እስከ 2026 ድረስ ሽያጩን ለማካሄድ እንደታቀደ የኢትዮጵያ የደን ልማት ዋና ደይሬክተር ከበደ ይማም ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
ኃላፊው ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከ2018 እስከ 2022 ምን ያህል ትሸጣለች የሚለው ጥናት ሲጠናቀቅ ይፋ እንደሚሆንም አመላክተዋል።
በኦሮሚያ ክልል ካለው ደን 40 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ካርበን ለመሸጥ እየተሠራ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X