- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የኢትዮጵያ ፋሽን ፈተና፦ ያገለገሉ ልብሶች /ቦንዳ/ ገበያ

የኢትዮጵያ ፋሽን ፈተና፦ ያገለገሉ ልብሶች /ቦንዳ/ ገበያ
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የፋሽን ኢንደስትሪ ፈተና መልኩ እንዲህ ነው “ድሮ የቦንዳ ልብሶችን ሰው ተሸማቆ ነበር የሚገዛው [...] አሁን ግን ትልልቅ ሞሎች ላይ የቦንዳ ልብሶች ይሸጣሉ።” ስትል ዲዛይነር ኢክራም መሐመድ ነግራናለች።
ከዚህ መውጫው መንገድ ደግሞ የህንድ ምሳሌ ነው። "የኢትዮያ ታምርት ፅንሰ ሃሳብን ማስረፅና በኢትዮጵያ ምርት የምንኮራበት ሁኔታ መመቻቸት አለበት፣” ሲል በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ፋሽንና ጨርቃ ጨርቅ ኢንስቲትዩ አፓረል ዲን ቢኒያም ሰለሞን ነግሮናል።
በዚህ The Rising South የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት በሞስኮ የሚካሄደውን አፍሮ ፋሽን ሳምንት 2025 መነሻ አድርገን ከባለሙያዎቹ ጋር ዕድልና እንቅፍቶችን አንስተን በሰፊው ተወያይተናል።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ AfripodsDeezerPocket CastsPodcast AddictSpotify
አዳዲስ ዜናዎች
0