የካሳቫ ስታርች ምርት የመድኃኒትነት አዋጭነት ጥናት ለጤና ሚኒስቴር ቀረበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየካሳቫ ስታርች ምርት የመድኃኒትነት አዋጭነት ጥናት ለጤና ሚኒስቴር ቀረበ
የካሳቫ ስታርች ምርት የመድኃኒትነት አዋጭነት ጥናት ለጤና ሚኒስቴር ቀረበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.07.2025
ሰብስክራይብ

የካሳቫ ስታርች ምርት የመድኃኒትነት አዋጭነት ጥናት ለጤና ሚኒስቴር ቀረበ

ጥናቱን ያቀረቡት የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት እና የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት በጋራ በመሆን ነው፡፡

ምርምሩ በኢትዮጵያ ለሚመረቱ የፋርማሱቲካል፣ የምግብ እና ሌሎች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ምርቶች ካሳቫ ስታርችን በግብዓትነት እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚጠቁም እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬህይወት አበበ እንደ ካሳቫ የመሳሰሉ የሀገር ውስጥ የግብርና ግብዓቶችን በምርምር እና በገበያ ትስስር ወደ አዋጭ የፋርማሱቲካል ግብዓቶች መቀየር የጎላ አስተዋጻኦ እንዳለው ገልጸዋል። "መንግሥት የሀገር ውስጥ ፋርማሱቲካል ምርትን ለማሳደግ ባለው ቁርጠኝነት ከጥቂት ዓመታት በፊት ከፍተኛ እድገት የታየ ሲሆን በዚህም 8 በመቶ ብቻ ከነበረው የመንግሥት የመድኃኒት ገበያ ድርሻ የሀገር ወስጥ የፋርማሱቲካል ምርት የገበያ ድርሻ ወደ 41 በመቶ አድጓል” ብለዋል፡፡

ጥናቱ ያመላከታቸው ጥቅሞች፦

🟠 ከ50% በላይ የኢንቨስትመንት ትርፍ፣

🟠 ከ117 በላይ አዳዲስ ቀጥተኛ የሥራ ዕድል፣

🟠 ከ35 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ማድረግ፣

🟠 ከ90 በመቶ በላይ ከውጭ የሚገባውን ስታርች ማስቀረት፡፡

“በጥናትና ምርምር ማስረጃ ላይ የተመሠረተ ልማት ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ፣ የሀገር ውስጥ የፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማብቃት እና ሀገራዊ ግቦችን ለመደገፍ ያስችለናል" ሲሉ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ተናግረዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከወላይታ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የካሳቫ ስታርች ምርትን ለፋርማሱቲካል ዘርፉ በስፋት ጥቅም ላይ ለማዋል ምርምር እና ቴክኖሎጂ እያዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየካሳቫ ስታርች ምርት የመድኃኒትነት አዋጭነት ጥናት ለጤና ሚኒስቴር ቀረበ
የካሳቫ ስታርች ምርት የመድኃኒትነት አዋጭነት ጥናት ለጤና ሚኒስቴር ቀረበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.07.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0