የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፦ የሕዝብ ድጋፍ እንጂ፤ የውጭ ዶላር ውጤት አይደለም
10:38 18.07.2025 (የተሻሻለ: 10:44 18.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፦ የሕዝብ ድጋፍ እንጂ፤ የውጭ ዶላር ውጤት አይደለም
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በቅርቡ የሰጡትን አስተያየት ውድቅ ያደረጉት የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓርላማ አባልና በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ሙሉጌታ ደበበ "ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን የገንዘብ ድጋፍ የተገነባ ግድብ ነው" ብለዋል።
ግድቡ በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገለት እና ግብጽ የምታገኘውን ውሃ በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል የሚለውን የትራምፕ ንግግር በተመለከተ ፕሮፌሰሩ አጽንዖት ሰጥተው ሲናገሩ፡-
“ውሃውን መቆጣጠር እና ፍሰቱን ወጥ ያደርገዋል እንጂ...ግብጽም ሆነ ሱዳን በዓባይ ጎርፍ አይጎዱም” ብለዋል።
ሕዳሴ ግድብ ሁሉም ዜጎች፤ “ወጣቱ፣ አዛውንቱ፣ ባለጸጋውና ያጠራቸውም” በአቅማቸው ባደረጉት አስተዋጽኦ የተገነባ የኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ምልክት ነው ሲሉ ምሁሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
“አፍሪካውያን እንደ ሕዝብ ሊከበሩ ይገባል” በማለትም ንግግራቸውን አጠናቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X